1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚ

የኢትዮጵያ የጋራ የገቢ ማከፋፈያ ቀመር ሊሻሻል ነው

ሰኞ፣ ግንቦት 5 2011

በፌዴራልና በክልል መንግስታት መካከል ያለው የጋራ የገቢ ማከፋፈያ ቀመር ግልፅነት የጎደለው እንደነበር የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወይዘሮ ኬርያ ኢብራሂም ተናገሩ። ለ9ኛ ጊዜ ተሸሽሎ ጥቅም ላይ የዋለው የድጎማ ቀመርም በበጀት አስተዳደርን ክፍፍል ላይ የታሰበውን ያህል ችግር ፈች ስላልነበር ሁለቱም ቀመሮች ሊሻሻሉ ነው ተብሏል።

https://p.dw.com/p/3IQYW
Diskussion über Bundeshaushalt von Äthiopien in Addis Abeba
ምስል DW/Solomon Muchie

የኢትዮጵያ የጋራ የገቢ ማከፋፈያ ቀመር ሊሻሻል ነው

ላለፉት 22 አመታት ሲያገለግል የነበረው በፌዴራል እና በክልል መንግስታት መካከል ያለው የጋራ የገቢ ማከፋፈያ ቀመር  ሁሉም እንዲያውቀው ከማድረግ አንጻር ግልጽነት ያልነበረው እንደነበር የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ኬርያ ኢብራሂም ተናገሩ፡፡ከዚህ በተጨማሪ ለ 9ኛ ጊዜ ተሸሽሎ ጥቅም ላይ የዋለው የድጎማ ቀመርም በበጀት አስተዳደርን ክፍፍል ላይ የታሰበውን ያህል ችግር ፈች ስላልነበር ሁለቱም ቀመሮች ሊሻሻሉ ነው ተብሏል፡፡

ከ15 አመታት በፊት ጥቅም ላይ ይውሉ የነበሩት የድጎማ ቀመር መስፈርቶች የድህነት መጠን ፡ የህዝብ ቁጥር እና የገቢና ወጭ ጥምርታ የነበሩ ሲሆኑ ፡ አሁን ላይ ግን የልማት ስራዎች ዋነኛ መስፈርቶች መሆናቸውንም ለማወቅ ችለናል፡፡የህዝብ ቁጥር በተዘዋዋሪ ካልሆነ በቀጥታ መስፈርት አለመሆኑንም ከክልሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር በተደረገው የግጽነት መድረክ ላይ ተገልጽዋል፡፡የክልሎችን የበጀት አቅም ለማመጣጠን ፡ ክልሎች ለህዝቦች ተመጣጣኝ መንግስታዊ አገልግሎት እንዲሰጡ የታለመለት የድጎማ ቀመር መሰረታዊ የሚባል ክፍተት የነበረበት ነው ተብሏል፡፡
ሰለሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ