1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ የግድግዳ ጡፍ

ዓርብ፣ ታኅሣሥ 10 2007

ኢትዮጵያ ውስጥ የምዕራብ ሀገራቱ አይነት የግድግዳ ጡፍ ብዙም የተለመደ ባይሆንም፤ ድርጊቱ ኢትዮጵያ ውስጥም አለ። ስለ ግራፊቲ ይዘት እና ዓላማ በዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት እንቃኛለን።

https://p.dw.com/p/1E7Xa
Behulum Graffiti
ምስል Behulum Graffiti

ሰዎች ግራፊቲን ማንነታቸውን ሳያሳውቁ ሀሳባቸውን በድብቅ ለመግለፅ ከሚጠቀሙበት መንገድ አንዱ ነው። ኢትዮጵያ ውስጥ የግድግዳ ጡፎች በብዛት የሚስተዋሉት በትምህርት ቤቶች አካባቢ ነው እና የዛሬው ዝግጅት ወደ የአዲስ አበባ ዮንቨርስቲ ይመራናል። በአዲስ አበባ ዮንቨርስቲ የህግ ተማሪ የሆነው ናሆም ተክለ ወልድ ካነበባቸው የግድግዳ ጡፎች መካከል ጥቂቱን አካፍሎናል።

ምንም እንኳን አንዳንድ ጡፎቹ አዝናኝ ቢሆኑምና የፀሀፊው ማንነት ቢታወቅ በፀሀፊው ላይ የግድ አሉታዊ ተፅዕኖ ባያስከትሉም ፤ ስለ ፃሀፊው ማንነት የሚያውቅ ወይም እሱን በአይኑ የሚያይ ጥቂት ነው። በአዲስ አበባ ዮንቨርስቲ የስነ ፁሁፍ እና ፎክሎር መምህር የሆኑት ዶክተር ፍቃደ አዘዘ ፤ የግድግዳ ጡፍ ከግድግዳ ያለፈ ነው ይላሉ።የዮንቨርስቲ ተማሪው ናሆምም ይሁን መምህር ፍቃደ እንደገለፁልን ግራፊቲ፤ የአንደ ሰው ሀሳብ መግለጫ ብቻ ሳይሆን ሰዎች እንደ መወያያ መድረክ የሚጠቀሙበትም ገፅ ነው።

Hauptcampus der Universität Addis Abeba AAU
ምስል DW

በርካታ ሰዎች፤ የግድግጣ ጡፍ የሚፅፉት ፤ ስሜታቸውን ለመግለፅ እንደሆነ ይናገራሉ። ስሜታቸውን ለምን በአደባባይ እና በፁሁፍ እንደሚገልፁ ደግሞ የስነ ፁሁፍ መምህሩ አብራርተውልናል። በዚሁ ከፍተኛ ተቋም በተማሪነት እና በመምህርነት ረዥም ዓመታት ያስቆጠሩት ዶክተር ፍቃደ፤ በአጠቃላይ ስለ ኢትዮጵያ ግድግዳ ጡፎች መሰረት እና አመጣጥ በቂ ጥናት አልተደረገም ይላሉ። የግድግጣ ጡፍ ርዕሶቹም እንደገዢው መንግሥት እንደሚለያዩ ነው የገለፁልን፤ ዝግጅቱን ለማድመጥ ከታች ይመልከቱ።

ልደት አበበ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ