1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ የፀጥታው ምክር ቤት ተለዋጭ አባልነት

ረቡዕ፣ ሰኔ 22 2008

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ «መድረክ» በአጭሩ ኢትዮጵያ ይህን ቦታ ማግኘቷን ፋይዳ ቢስ ሲለው የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ ደግሞ ኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶችን አያያዝን ለማሻሻል ትጠቀምበት ብሏል ።

https://p.dw.com/p/1JFrF
Symbolbild UN-Sicherheitsrat
ምስል picture-alliance/dpa/A. Gombert

[No title]

ኢትዮጵያ በተመድ የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት የተለዋጭ አባልነት መቀመጫ ማግኘቷ በአገር ውስጥ ከሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ድርጅቶች እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በኩል ልዩ ልዩ አስተያየቶች እየተሰነዘሩበት ነው። የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ(«መድረክ» በአጭሩ) ኢትዮጵያ ይህን ቦታ ማግኘቷን ፋይዳ ቢስ ሲለው፤ የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ ኢራፓ ደግሞ ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶችን አያያዝን ለማሻሻል ትጠቀምበት ብሏል። የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ ሊቀመንበር በበኩላቸው በዙር የሚደርሰውን ይህን ቦታ ኢትዮጵያ ማግኘቷ ትርጉም የለውም ብለዋል ።አስተያየቶቹን ያሰባሰበው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር ዝርዝሩን ልኮልናል ።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ