1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 8 2009

መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መደነንገጉ እና ለአዋጁም ማስፈፀሚያ ብዙዎች አፋኝ የሚሏቸውን መመሪያዎች ማውጣቱ በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ስጋት ውስጥ ከቷል ።

https://p.dw.com/p/2ROfM
Deutschland Demonstration in Berlin gegen Verletzungen der Menschenrechte in Äthiopien
ምስል DW/Y. H. M. Korri

የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ቀዉስና ኢትዮጵያዉን በጀርመን

ርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን  በሀገራቸው ጉዳይ ላይ

የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ዜጎችን በያሉበት እያነጋገረ  ነው ። ከኢትዮጵያ ውጭ የሚገኙ ዜጎች በአሁኑ ጊዜ ከሚወያዩባቸው እና ከሚጨነቁባቸው ጉዳዮች ውስጥ ሀገራቸው የምትገኝበት ሁኔታ በዋነኛነት ይጠቀሳል ። ርቀው ቢገኙም ዞሮ መግብያቸው በሆነችው በሀገራቸው የተከሰተው የፖለቲካ ቀውስ በእጅጉ እንደሚያሳስባቸው እና የወገናቸውም ጉዳይ እንደሚቆረቁራቸው በየአጋጣሚው ይገልፃሉ ። እዚህ ጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውን ሀገራቸው አሁን ስለ ምትገኝበት ሁኔታ የሚሰማቸውን  እና ለሀገራቸው ሰላም ይበጃል የሚሏቸው መፍትሄዎች አጋርተውናል ። በዛሬው አውሮፓ እና ጀርመን ዝግጅታችን ተቀናብሯል ። አዘጋጅዋ ኂሩት መለሰ ታቀርብልናለች  
በተለያዩ የጀርመን ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ስለ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ቀውስ እና መፍትሄው  ለዶቼቬለ ከሰጡት አስተያየት የተወሰደውን ነው የሰማችሁት ።
በኢትዮጵያ የተለያዩ ከተሞች ከተካሄዱት ተቃውሞች በኋላ መንግሥት የወሰዳቸው ጠንካራ የሚባሉ  እርምጃዎች ዜጎችን ማሳሳበቸው ቀጥሏል ። በተለይ መንግሥት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መደነንገጉ እና ለአዋጁም ማስፈፀሚያ ብዙዎች አፋኝ የሚሏቸውን መመሪያዎች ማውጣቱ በሀገር ውስጥ ብቻ ሳይሆን በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ስጋት ውስጥ ከቷል ። ዶቼቬለ በዚሁ ጉዳይ ላይ ያነጋገራቸው ጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያን  ስለ ሀገራቸው በሚሰሙት እና በሚያዩት ማዘናቸውን እና መቆጨታቸውን ነው የተናገሩት ።
በርሊን ነዋሪ የሆኑት እና አቶ በላይነህ ተሾመ የሰጡት አስተያየት ነበር ።ጀርመን ሲኖሩ 28 ዓመት እንደሆናቸው የሚናገሩት የማንሀይም ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ አሳየሽ ሮይሽል የኢትዮጵያን ሁኔታ በቅርብ ይከታተሉ ። በመንፈስም ከኢትዮጵያ ተለይተው እንደማያውቁ የሚናገሩት ወይዘሮ አሳየሽ በሚሰሙት እና በሚያዩት ከሀዘንም በላይ ነው የተሰማኝ ይላሉ።በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሀገሪቱ ይፈፀማል የሚባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዲቆም ለኢትዮጵያ መንግሥት ድጋፍ የሚሰጡ ምዕራባውያን መንግሥታት  ግፊት እንዲያደርጉ ደጋግመው ይጠይቃሉ ። ቀደም ካሉት ዓመታት አንስቶ ሲቀርብ የነበረው ይህ ጥያቄ ካለፈው አንድ ዓመት ወዲህ ይበልጥ ተጠናክሮ ቀጥሏል ። የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል በቅርቡ ኢትዮጵያን ከመጎብኘታቸው በፊት ይኽው ጥያቄ ከኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጅ ከሆኑ ጀርመናውያን የመብት ተሟጋቾች ቀርቦላቸው ነበር ። ይህን ጥያቄአቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ለማቅረብ በርሊን ከተገኙት መካከል የፍራንክፈርቱ ነዋሪ አቶ ደሳለኝ ከበደ ይገኙበታል ።አቶ ደሳለኝ ሜርክል በኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ሄደው ያስተላለፉት መልዕክት አቶ ደሳለኝ አርክቷቸዋል ።

Deutschland Demonstration in Berlin gegen Verletzungen der Menschenrechte in Äthiopien
ምስል DW/Y. H. M. Korri

በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው ኢትዮጵያውን ሀገራቸው አሁን የገባችበት የፖለቲካ ቀውስ የሚያስጨንቅ እና የሚያሳስብ  ጊዜ ሳይወሰድም መፍትሄ ሊፈለግለት የሚገባ መሆኑን ነው ያስገነዘቡት ።

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ