1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ የፖለቲካ አውድና የተቃዋሚ የፖለቲካ ቅሬታ  

ሐሙስ፣ ጥር 27 2013

በኦሮሚያ በተለያዩ አከባቢዎች የድጋፍ ሰልፍ ከመደረጉ በፊት በተደጋጋሚ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ጠይቀን ተከልክለናል ያሉት የፖለቲካ ድርጅቶች ሂደቱን የፖለቲካ ምህዳሩን የሚያጠብ ብለውታል።ምርጫ ቢቃረብም ለተቀናቃኝ የፖለቲካ ድርጅቶች የተመቻቸ አውድ አለመኖሩን የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲና የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ ፓርቲ አመራሮች ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/3otcy
Karte Äthiopien englisch

የኢትዮጵያ የፖለቲካ አውድና የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቅሬታ  

የኢትዮጵያ መንግስት ለገዢው ፓርቲ የሚሰጠውን ከለላና ነጻነት ለተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶችም መስጠት እንዳለበት የተቀናቃኝ የፖለቲካ ድርጅቶች አመራሮች ጠየቁ። ሰሞኑን በኦሮሚያ በተለያዩ አከባቢዎች የድጋፍ ሰልፍ ከመደረጉ በፊት በተደጋጋሚ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ጠይቀን ተከልክለናል ያሉት የፖለቲካ ድርጅቶች ሂደቱን የፖለቲካ ምህዳሩን የሚያጠብ ብለውታል።በተያዘው ዓመት ይከናወናል ተብሎ ቀነ ቀጠሮ የተያዘለት ብሔራዊ ምርጫ የሚካሄድበት ጊዜ ቢቃረብም ለተቀናቃኝ የፖለቲካ ድርጅቶች የተመቻቸ አውድ አለመኖሩንም የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ እና የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ ፓርቲ አመራሮች ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡
 

ስዩም ጌቱ

ኂሩት መለሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ