1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ-ጀርመን የምርምር እና የባህል ልዉዉጥ

ሐሙስ፣ መስከረም 22 2007

በጀርመን እና በኢትዮጵያ መካከል፤ ያለዉ የትምርት የምርምር እና የባህል ልዉዉጥ ግንኙነት እጅግ የቆየ መሆኑ ይታወቃል። በተለይ ከጎርጎረሳዉያኑ 1624 እስከ 1704 ከኖረዉ ጀርመናዊ ምሁር ሂዮብ ሩዶልፍ ጀምሮ እስካሁን ድረስ ያሉ ምሁራን በኢትዮጵያ ልዩ ልዩ ጥንታዊ ቅርሶች

https://p.dw.com/p/1DOsB

የብራና መጻሕፍት የቋንቋ የባህል የታሪክ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ ምርምርና ጥናት ስራቸዉ ይታወቃል። ይህ የምርምርና የባህል ልዉዉጥ የበለጠ እንዲልቅ በማሰብ ከጥቂት ዓመታት በፊት ጥናቱ በሁለቱም ሀገራት ላይ እንዲቀጥል የሀንቡርግ የባሕር ዳር እንዲሁም ደብረ ማርቆስ ዩንቨርስቲዎች የምርምር ስራዎቻቸዉን ለመለዋወጥ እና ተማሪዎች በሁለቱም ሀገራት ልምዶችን እንዲቀያየሩ ለማስቻል «ዓባይ የጥናት የምርምር ማዕከል» በሚል ባህር ዳር ዩንቨርስቲ ላይ ማዕከል ተቋቁማል። በለቱ ዝግጅታችን የዚህ ማዕከል መስራች በሐንቡርግ ዩንቨርስቲ ዶክተር ጌቴ ገላዩ እንዲሁም ሰሞኑን ለሥራ ጉብኝት ወደ ጀርመን በርሊን የመጡት በባህር ዳር ዩንቨርስቲ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ተስፋዬ ሽፈራዉን የለቱ ዝግጅታችን እንግዶች አድርገናል።