1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ገዳማት ይዞታ በእስራኤል

ሐሙስ፣ ጥር 9 2005

ከሰሃራ በታች ከሚገኙት አፍሪቃ ሃገራት በእስራኤል ገዳም እና ሌላም ይዞታ ያላት ብቸኛ ጥቁር አፍሪቃዊት አገር ኢትዮጵያ መሆንዋ ይታወቃል።

https://p.dw.com/p/17LeQ
ምስል AP
Nahost Israel Karwoche in Jerusalem
ምስል AP

የዴር- ሱልጣን ገዳም ጥሪ በሚል ርዕስ፤ ባለፈዉ ሳምንት  ባቀረብነዉ መሰናዶአችን ፤በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን እና በግብፅ ኮፕት ቤተክርስትያን መካከል በይዞታ ይገባናል ጥያቄ ምክንያት ገዳሙ መጠገን ባለመቻሉ በመፈራስ ላይ መሆኑን፤ ስለጉዳዩ ጥናታዊ ፊልም የሰሩ ጀርመናዊ የፊልም ስራ አዋቂ እና  አካባቢዉ ላይ የሚገኙትን የሃይማኖት አባቶችን አነጋግረን ዘገባ አስደምጠናል።ይህ ለዘመናት የቆየ ችግር መፍትሄዉ ምን ይሆን?  በእስራኤል የኢትዮጵያ ሌሎች ይዞታዎችስ በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ?  ከሰሃራ በታች ከሚገኙት አፍሪቃ ሃራት በእስራኤል ገዳም እና ሌላም ይዞታ ያላት ብቸኛ ጥቁር አፍሪቃዊት አገር ኢትዮጵያ መሆንዋ ይታወቃል። በስድስት ሀገራት አብያተ ክርስትያ የተያዘዉ የጎልጎታዉ  ዴር ሱልጣን ገዳም ዉዝግብ ከጀመረ ከ240 ዓመታት በላይ ማስቆጠሩን ባለፈዉ ሳምንት በቅድስት ሀገር እየሩሳሌም የኢትዮጳያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስትያን ገዳማት ሊቃነ-ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማትያስ መናገራቸዉ ይታወሳል።

መፍትሄዉ ምን ይሆን? በእስራኤል የኢትዮጵያ ገዳማትና ታሪካዊ ቦታዎችን ለማስጠበቅ የተቋቋመዉ ድርጅት የቦርድ ሊቀመንበር አቶ አለማየሁ ተስፋዪ፤ ድርጅታቸዉ የኢትዮጳያን ይዞታዎች ለማስጠበቅ በርካታ ጥረቶችን በማድረግ ላይ ነዉ ሲሉ ገልጸዋል። በተለይ የዴር ሱልጣንን ይዞታ በተመለከተ በፍርድ ቤት ሳይሆን በሚኒስትሮች ደረጃ የተቋቋመ ኮሚቴ ጉዳዩን እየተከታተለዉ መሆኑን ገልጸዋል።
በርግጥ ይህን ችግር በተመለከተ መፍትሄ ለማፈላለግ በእስራኤል የኮፕት ቤተክርስትያንን እና በኢትዮጵያ የእስራኤል ኤንባሲን ለማነጋገር ያደረግነዉ ጥረት አልተሳካም። በይፋ እንደሚታየዉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን እና በግብፅ ኮፕት ቤተ ክርስትያ መካከል ጠንካራ የሆነ ጥሩ መግባባት ያላቸዉ መሆኑ ነዉ። ለዚህ በምሳሌ ተጠቃሹ የግብፅ ኮፕት ቤተክርስትያን ፓትርያርክ ከዚህ ዓለም ሲለዪ ፍትሃቱን የመሩት የቀድሞዉ የኢትጵያዉ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ፓትርያርቅ አቡነ ጳዉሉስ ነበሩ። እየሩሳሌም የሚታየዉ የሁለቱ አብያተ ክርስትያን ግንኙነት ግን ከዚህ ገጽታ እጅግ የራቀ ሆኖ ነዉ ፤ እና ይህን እንዴት ይጣጣማል? ለሚለዉ፤ በቅድስት ሀገር እየሩሳሌም የኢትዮጳያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስትያን ገዳማት ተጠሪ ሊቃነ-ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ማትያስ  ጉዳዩ መልስ የሌለዉ ነዉ ብለዉናል።  
በሃይማኖት በሀገር ፍቅር ጸንተዉ በእየሩሳሌም ዴር ሱልጣን ገዳምን ይዞታ ለማስጠበቅ እና ለልጅ ልጅ ለማቆየት ትግል ላይ ያሉት መነኮሳት ህዝብ ሊደግፈን የሀገር ቅርስ በመሆኑም መንግስት መፍትሄ ሊያገኝልን ይገባል ሲሉ ጥሪአቸዉን ያሰማሉ። በእየሩሳሌም የሚገኙ የኢትዮጵያ ገዳማትን ይዞታ በተመለከተ በሁለት ተከታታይ ክፍል ቃለ ምልልስ በመስጠት የተባበሩንን ሁሉ በዝግጅት ክፍላችን ስም እናመሰግናለን። ሙሉዉን እንብር ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ

Erlöserkirche in Jerusalem
ምስል Dieter Vieweger
ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ