1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ጉዳይ በጀርመን ፖለቲከኛ እይታ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 22 2009

ኒማ ሞሳቫት በጀርመን ምክር ቤት የግራዎቹ ፓርቲ ተወካይ ፣ ጀርመን እና የአውሮጳ ኅብረት በኢትዮጵያ ህዝብን ተጠቃሚ የማያደርጉ አሠራሮች እንዲቀየሩ ጥረት እንዲያደርጉ ለዶይቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ ጠይቀዋል።

https://p.dw.com/p/2RzJd
Flüchtlinge auf Mittelmeer
ምስል picture-alliance/Bundeswehr/S. Hoder

Beri.Berlin ( Int Nima Movasat Mitglied des Deutschen Bundestages für die Linke) - MP3-Stereo

ጀርመን  እና የአውሮጳ ኅብረት ፣ ኅብረተሰቡን ተጠቃሚ የማያደርግ ፣ ከመሬቱ የሚያፈናቅል እና በሰላማዊ ሰልፈኞችም ላይ ተኩስ ከፍቶ የሚገድል ካሉት መንግሥት ጋር መሥራት የማይችሉበት ደረጃ ላይ እንደደረሱ አንድ የጀርመን ፖለቲከኛ አስታወቁ ። ይህን አሰተያየት የሰጡት ኒማ ሞቫሳት በጀርመን ምክር ቤት የግራዎቹ ፓርቲ ተወካይ ፣ ጀርመን እና የአውሮጳ ኅብረት በኢትዮጵያ ህዝብን ተጠቃሚ የማያደርጉ አሠራሮች እንዲቀየሩ ጥረት እንዲያደርጉ ለዶይቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ ጠይቀዋል። በርሳቸው አስተያየት ይህ ተግባራዊ ካልሆነ ከኢትዮጵያም ሆነ ከሌሎች የአፍሪቃ ሀገራት ወደ አውሮጳ የሚጎርፉ ስደተኞችን ማስቆም አይቻልም። የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል የጀርመን የህዝብ እንደራሴን ኒማ ሞሶቫትን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።