1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማኅበር 50ኛ ዓመት በዓል

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 29 2011

የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማኅበር (ኢጋማ) የተመሰተተበትን 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤሊዩ በስካይ ላይት ሆቴል አከበረ። ማኅበሩ ባለፉት የ50 ዓመታት ዕድሜው የጋዜጠኝነት ሞያን ለማጎልበት ጥረት ማድረጉን ጠቅሷል።

https://p.dw.com/p/3I5d4
Äthiopien - Journalistenverband feiert 50jähriges Jubiläum
ምስል DW/G. Tedla Hailegiorgis

ኢጋማ 50ኛ ዓመት በዓሉን አከበረ

የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማኅበር (ኢጋማ) የተመሰተተበትን 50ኛ ዓመት የወርቅ ኢዮቤሊዩ በስካይ ላይት ሆቴል አከበረ። ማኅበሩ ባለፉት የ50 ዓመታት ዕድሜው የጋዜጠኝነት ሞያን ለማጎልበት ጥረት ማድረጉን ጠቅሷል። ኾኖም «በኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት እንዲከበር በመታገል በኩል» የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ማኅበር «ኢጋማ የሚጠበቅበትን ያህል እንዳልሠራ አይካድም» ሲሉ የማኅበሩ ፕሬዚደንት መሠረት አታላይ ተናግረዋል። «ፖለቲከኛ ተጽዕኖዎችን በገለልተኝነት መንፈስ አለመጋፈጡ ኹሌም በቊጭት የምናወሳው የኢጋማ ደካማ ጎን ነው» ብለዋል። በሥፍራው የተገኘው የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ በሞያው የተሠማሩ የተለያዩ ሰዎችን አነጋግሮ ቀጣዩን ዘገባ ልኮልናል። 

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ