1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ጥንታዊ አርበኞች ማሕበር 75ኛ ዓመት

ረቡዕ፣ ሚያዝያ 26 2008

አሜሪካዊዉ አዉሮፕላን አብራሪ ኮሎኔል ጆን ሮብንሰን ለኢትዮጵያ ነፃነት ከኢትዮጵያዉያን ጎን ሆነዉ ከተዋጉ የዉጪ ዜጎች አንዱ ነበሩ። በጦርነቱ ወቅት ብዙ ኢትዮጵያዉያን ከተሰዉበት አንዱ ደግሞ «አመፀኛዉ» የተባለዉ ዋሻ ነዉ።

https://p.dw.com/p/1IiNz
ምስል DW/Y. G. Egziabher

[No title]

የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማሕበር የተመሠረተበት 75ኛ ዓመት በዓል ነገ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ይከበራል። የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች ታሪክ ኢትዮጵያን ከፋሽስት ኢጣሊያ ወረራ ነፃ ለማዉጣት የተደረገዉ ዉጊያ፤ ትግልና መከራ ጋር በእጅጉ የተቆራኘ ነዉ። ኢትዮጵዉያን ከወራሪዉ ጦር ጋር ባደረጉት ዉጊያ ቁጥራቸዉ አነስተኛ ቢሆንም የዉጪ ተወላጆች ከኢትዮጵያዉን ጎን ሆነዉ ተፋልመዋል። አሜሪካዊዉ አዉሮፕላን አብራሪ ኮሎኔል ጆን ሮብንሰን ለኢትዮጵያ ነፃነት ከኢትዮጵያዉያን ጎን ሆነዉ ከተዋጉ የዉጪ ዜጎች አንዱ ነበሩ። በጦርነቱ ወቅት ብዙ ኢትዮጵያዉያን ከተሰዉበት አንዱ ደግሞ «አመፀኛዉ» የተባለዉ ዋሻ ነዉ። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ የኮሎኔል ሮብንሰንን እና የአመፃኛዉ ዋሻን ታሪክ ባጭሩ ይተርክልናል።

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሐመድ