1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ

ሰኞ፣ መስከረም 27 2006

ዶክተር ነጋሶ እንደሚሉት እሳቸዉም ሆኑ ዛሬ የአስራ-ሁለት ዓመታት ዘመነ-ሥልጣናቸዉ ያበቃዉ አቶ ግርማ ወልደ ጊዮርጊዮስ እንደፕሬዝዳትነት የሚጠበቅባቸዉን አላደረጉም።ዛሬ በፕሬዝዳትነት የተመረጡት ዶክተር ሙላቱ ተሾመም ከእስካሁኖቹ የተለዩ ይሆናሉ ብለዉ አይጠብቁም።ምክንያት?

https://p.dw.com/p/19vnm
Mulatu Teshome speaks after being sworn in as Ethiopia's new president in Addis Ababa on October 7, 2013. Ethiopia's parliament elected Mulatu Teshome to be the country's new president today, for a six-year term in a largely symbolic and ceremonial post. AFP PHOTO / Elias Asmare (Photo credit should read ELIAS ASMARE/AFP/Getty Images
ምስል Elias Asmare/AFP/Getty Images

ኢትዮጵያ ከደርግ ሥርዓት ዉድቀት በኋላ (አዲስ በፀደቀዉ ሕገ-መንግሥት መሠረት ሁለተኛዉ ፕሬዝዳት ዛሬ ተሰናብቶላት፥ ሠወስተኛዉ ተመርጦላታል።ዛሬ የተሰናበቱት የፕሬዝዳት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ የአስራ-ሁለት ዓመታት ምግባር፥ አዲስ የተመረጡት የፕሬዝዳት ሙላቱ ተሾመ ማንነት፥ ፕሬዝዳት አጠቃላይ ሐላፊነትና የምርጫዉ ሒደት ያፍታ ቅኝታችን ትኩረት ነዉ።ዝግጅታችን ከትንታኔ ይልቅ በቃለ ምልልስ ላይ ያተኮረ ነዉ።አብራችሁን ቆዩ።

ዊኪፔዲያ የተሰኘዉ እዉቅ ዓለም አቀፍ አምደ-መረብ በዘገበዉ መሠረት ታሕሳስ 1917 ነዉ የተወለዱት።ፕሬዝዳት ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ፥ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ትምሕርት ቤት መንፈሳዊ፥ በቀድሞዉ ተፈሪ መኮንን ትምሕር ቤት ደግሞ ዘመናዊ ትምሕርታቸዉን ተከታትለዋል።በ1936 ከጦር ትምሕርት ቤት በምክትል መቶ አለቅነት ማዕረግ ከተመቀረቁ በሕዋላ በኢትዮጵያ አየር ሐይል፥ ያኔ የንግድ፥ የኢንዱስትሪና ዕቅድ ወይም ፕላን ይባል በነበረዉ መስሪያ ቤት በሐላፊነት ሠርተዋል።

ከ1947 እስከ 1950 ግድም ድረስ በኤርትራ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሺን ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት፥ ከዚያ በሕዋላ ደግሞ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ሐላፊ ሆነዉ አገልግለዋል።በ1953 የኢትዮጵያ ዘዉዳዊ ምክር ቤት (የሕግ መምሪያ) እንደራሴ ሆነዉ ሲመረጡ ፖለቲካዉን ተቀየጡ።በዚሕም ሰበብ ይመስላል ከፕሬዝዳት ግርማ በፊት የፕሬዝዳትነቱን ሥልጣን ይዘዉ የነበሩት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ፕሬዝዳት ግርማን ለሰወስቱም ሥርዓቶች ያገለገሉ ይሏቸዋል።

በኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት መሠረት ፕሬዝዳቱ ከሥነ-ሥርዓታዊ ጉዳዮች ያለፈ ሥልጣን በርግጥ የለዉም።በዚያዉ ሕግ መሠረት ፕሬዝዳንቱ ከፖለቲካ ፓርቲዎች፥ ከተለያዩ ማሕበራት አባልነት ነፃ ሆኖ፥ ሐገሪቱንና ሕዝቡን በገለልተኝነት ማገልገል አለበት።ይሑንና በኢትዮጵያ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብቸኛዉ የተቃዋሚዉ (የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ) እንደራሴ አቶ ግርማ ሰይፉ እንደሚሉት ፕሬዝዳት ግርማ ያላቸዉን ትንሽ ሥልጣንም ቢሆን በተገቢዉ መንገድ አልተጠቀሙበትም።

አይ ኤስ ኤስ በሚል ምሕፃረ ቃል የሚጠራዉ ጥናት ተቋም ባልደረባ አቶ ሐሌሉያ ሉሌም ፕሬዝዳንት ግርማ ከዕድሜ መግፋት፥ ከጤና መታወክም በላይ የፖለቲካዉ ጫና የሚጠበቅባቸዉን ያክል እንዳይሰሩ ተፅዕኖ አሳድሮባቸዋል ባይ ናቸዉ።

የቀድሞዉ ፕሬዝዳትና ያሁኑ የኢትዮጵያ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት ባጭሩ) ሊቀመንበር ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳም በዚሕ ይስማማሉ።

ዶክተር ነጋሶ እንደሚሉት እሳቸዉም ሆኑ ዛሬ የአስራ-ሁለት ዓመታት ዘመነ-ሥልጣናቸዉ ያበቃዉ አቶ ግርማ ወልደ ጊዮርጊዮስ እንደፕሬዝዳትነት የሚጠበቅባቸዉን አላደረጉም።ዛሬ በፕሬዝዳትነት የተመረጡት ዶክተር ሙላቱ ተሾመም ከእስካሁኖቹ የተለዩ ይሆናሉ ብለዉ አይጠብቁም።ምክንያት? አንጋፋዉ ፖለቲከኛ ይቀጥላሉ።

ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ከቻይና እስከ ዩናትድ ስቴትስ በሚገኙ ከፍተኛ የትምሕርት ተቋማት ተምረዋል።ኢሕአዲግ ሥልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ በተለያዩ መስሪያ ቤቶች በምክትል ሚንስትርነት፥ በሚንስትርነት፥ በፌደሬሽን ምክር ቤት እንደራሴነት፥ በአምባሳደርነትም አገልግለዋል።የገዢዉ የኢሕአዲግ ተጣማሪ ፓርቲ የኦሮሞ ሕዝብ ዴምክራሲያ ድርጅት (ኦሕዴድ) ከፍተኛ ባለሥልጣንም ናቸዉ።

ዶክተር ሙላቱ በሙሉ ድምፅ ነዉ የተመረጡት።ብቸኛዉ የተቃዋሚ ፓርቲ እንደራሴ አቶ ግርማ ሠይፉም ደግፈዋቸዋል።አቶ ግርማ ምን አንጠብቅ ለሚለዉ ጥያቄ መልስ አላቸዉ።ግን «ተስፋ»-የሚል መልስ።

የምርጫዉ ሒደት ዛሬም እንደ እስከ ዛሬዉ አነጋጋሪ ነበር።የጠቅላይ ሚንስትር ሐይለ ማርያም ደሳለኝ ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸዉ ረዳ ከምርጫዉ በፊት ምርጫዉ ሕገ-መንግሥታዊዉን ደንብ የጠበቀ እንደሆነና እንደሚሆን አስታዉቀዉ ነበር።

አቶ ግርማ ሰይፉ ግን ሒደቱን «ኮሚንስታዊ» በማለት ያጣጥሉታል።

በይፋ እንደሚታወቀዉ የቀድሞዎቹ ሁለት ፕሬዝዳቶችም ሆኑ ዛሬ የተመረጡት ሰወስተኛዉ ፕሬዝዳት የኦሮሞ ብሔር ተወላጆች ናቸዉ።የብሔር ፖለቲካን የሚከተለዉ ኢሕአዴግ ለፕሬዝዳትነት የኦሮሞ ተወላጆችን በተከታይ መሾሙን አቶ ሐሌሉያ ሉሌ እንደሚሉት ገዢዉ ፓርቲ እንዳልተፃፈ ሕግ ሳይከተለዉ አልቀረም።

በፖለቲካ አቋም አቶ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ ለፕሬዝዳትነት ከመመረጣቸዉ በፊት በግል ተወዳድረዉ የምክር ቤት እንደራሴ ነበሩ እንጂ በይፋ የፖለቲካ ፓርቲ አባል አልነበሩም።ዶክተር ነጋሶ ግን ኋላ ሥልጣን ለቀቁ እንጂ ልክ እንደ ዶክተር ሙላቱ ሁሉ የኦሕዴድ ከፍተኛ ባለሥልጣን ነበሩ።ነጋሽ መሐመድ ነኝ ቸር ያሰማን።

Autor: Ludger Schadomsky Copyright: Ludger Schadomsky/DW Titel: Das Parlamentsgebäude in Äthiopiens Hauptstadt Addis Abeba Thema: Am 23.Mai wählen 32 Millionen registrierte Äthiopier ein neues Parlament sowie die Vertreter der State Councils. 547 Sitze sind zu vergeben. Die - umstrittene - Einwohnerzahl der 9 + 2 Regionen Äthiopiens bestimmt die Zahl der Sitze. Schlagwörter: Parlamentswahl Äthiopien 2010, Parlament, Sitze
ምስል DW
Girma_DPA.jpg President of Ethiopia, Girma Wolde Giorgis, arrives at Fiumicino airport in Rome on Saturday, 12 March 2005. EPA/STR +++(c) dpa - Report+++
ምስል picture-alliance/ dpa

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ