1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮ-ኤርትራ የሰላም ኮንፍረንስ በአዲግራት

ሐሙስ፣ ጥር 16 2011

በኢትዮጵያና ኤርትራ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ትኩረቱ ያደረገ ኮንፈረንስ ዛሬ በዓዲግራት ከተማ ሲካሄድ ውሏል፡፡ በኮንፈረንሱ ከተለያዩ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲዎች የታደሙ ምሁራን፣ ኤርትራውያን የሲቪክ ማሕበራት ተወካዮች፣ የዓዲግራት ከተማ ነዋሪዎች እና ሌሎች ተሳታፊዎች ተገኝተዋል፡፡

https://p.dw.com/p/3C7f6
Äthiopien und Eritrea Frieden Logo
ምስል DW/S. Fekade

የኢትዮ-ኤርትራ የሰላም ኮንፍረንስ በአዲግራት

በዛሬው ኮንፈረንስ የመነሻ ፅሑፍ ያቀረቡት በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ  ምሁር የሆኑት አቶ አለሙ አስፋው የተጀመረውን ግንኙነት አደጋ ላይ ሊጥሉ የሚችሉ አጋጣሚዎች መኖራቸውን ጠቁመዋል፡፡ ምሁሩ ከጠቀሷቸው ፈተናዎች መካከል የሀገራቱ መሪዎች ባህርያት ይገኝበታል፡፡ እንደ ምሁሩ ገለፃ በተለይም በኤርትራ ወገን የፕሬዝዳንቱ የግል ባህሪ በሀገራቱ ግንኙነት ላይ ጫና የመፍጠር እድሉ ከፍተኛ ነው፡፡

ሌላው የህዝብ ለህዝብ ኮንፈረንሱ ተሳታፊ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ መምህሩና የዓረና ሉአላዊነትና ዴሞክራሲ ፓርቲ ሊቀ መንበር አቶ አብርሃ ደስታ በሁለቱ ሀገር ህዝቦች መካከል 'ምንም ጠብ የለም' ብለዋል፡፡ በመሪዎቹ በኩል የተደረሰውን የሰላም ስምምነት በማድነቅ፡ በቀጣይነት የስምምነቱ ይዞታ ለህዝብ ይፋ ሊደረግ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ከኤርትራውያን ወገን የሆኑት "የሲቪል ማሕበረሰብ ኤርትራ" ተወካይ አቶ ዳዊት ይብራህ ለሁለቱ ሀገራት ዘላቂ ሰላም የሁለቱ ሀገራት ህዝቦች ተሳትፎ ከፍተኛ መሆኑ ገልፀዋል፡፡

ሚሊዮን ሃይለስላሴ 

ተስፋለም ወልደየስ 

እሸቴ በቀለ