1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮ ጀርመን ስፖርት እና ባሕል ፌስቲቫል

ቅዳሜ፣ ግንቦት 26 2009

13 የጀርመን እግር ኳስ ቡድኖች የሚሳተፉበት ውድድር  «የኢትዮ ጀርመን ስፖርት እና ባሕል ፌስቲቫል» በሚል በርሊን ከተማ ውስጥ ቅዳሜ ግንቦት 26 ቀን፣ 2009 ዓ.ም. ተጀምሯል።  ፌስቲቫሉ እስከ ነገ ድረስ የሚቀጥል ነው።

https://p.dw.com/p/2e5lG
Deutschland äthiopisch - deutsches Sportfest in Berlin
ምስል DW/Y. Hailemichael

«የኢትዮ ጀርመን ስፖርት እና ባሕል ፌስቲቫል» ያደረግነውን ቃለ መጠይቅ እናሰማችሁ። 13 የጀርመን እግር ኳስ ቡድኖች የሚሳተፉበት ውድድር በርሊን ከተማ ውስጥ ዛሬ ተጀምሯል።  ፌስቲቫሉ እስከነገ ድረስ የሚቀጥል ነው። የዘንድሮው ውድድር 21ኛው ዙር እንደሆነ የተገለጠ ሲሆን፤ በፌስቲቫሉ ላይ በኢትዮጵያ ስፖርት እጅግ የሚታወቁት አቶ ፍቅሩ ኪዳኔን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው ሰዎች እና ደጋፊዎች ተገኝተዋል። በቦታው የሚገኘው የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ሚካኤልን ስቱዲዮ ከመግባቴ አስቀድሞ በስልክ አነጋግሬው ነበር። በውድድሩ ሥፍራ  ያለውን ድባብ በመግለጥ ይጀምራል። 

ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ማንተጋፍቶት ስለሺ