1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢንተርኔት አገልግሎትና ፈተናው፣

ረቡዕ፣ ኅዳር 18 2006

ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት መረጃ አገልግሎት ማግኛ ድር (WWW)የተሰኘው ድርጅት መሥራች፣ ብሪታንያዊው ሳይንቲስት፣ ሰር ቲሞቲ በርነርስ ሊ፤ ይኸው በይፋ መረጃ አቅራቢ የሆነው የኢንተርኔት «ድር» ቁጥጥርና ቅድመ ምርመራ እያየለ መምጣቱ ለወደፊቱ

https://p.dw.com/p/1APgm

የዴሞክራሲ ይዞታ አደጋ የሚደቅን ነው በማለት ባለፈው ሳምንት ማለቂያ ላይ ማስጠንቀቃቸው የሚታወስ ነው። ቲሞቲ በርነርስ ሊ ፣ ከ 23 ዓመት በፊት የመሠረቱትን ን ድርጅት ፣አንዳንድ መንግሥታት የሥጋት ምንጭ አድርገው እንደሚመለከቱትም አስታውቀዋል። በኢነተርኔት ድር ላይ ያንዣበበውን አደጋ ለመቋቋም ተጠቃሚዎች የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎችስ ምን ዓይነት ድርሻ ማበርከት ይችላሉ? ተክሌ የኋላ የድርጅቱን ዋና ጉዳይ ፈጻሚ ANNE JELLEMA ን በማነጋገር ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።

Symbolbild Sicherheit im Internet
ምስል picture-alliance/dpa

ሰር ቲም በርነርስ ሊ በዓመታዊው ዘገባቸው ላይ እንዳስረዱት ከሆነ በ WWW የኢንተርኔት ድር ፤ ግልጽ የሆነ አሠራርና ነጻነት፤ በከፍተኛ ደረጃ ለህዝብ አገልግሎት በመስጠት ማለፊያ ስም ያተረፈች ሀገር ስዊድን ከዚያም በሁለተኛነት ኖርዌይ መሆኗን ገልጸዋል። ብሪታንያና ዩናይትድ ስቴትስ በ 3ኛ ና 4ኛ ደረጃ ይከተላሉ። ዓለም አቀፉ የኢንተርኔት ድር ድርጅት፤ (World Wide Web Foundation )ነጻ «የኦንላይን » አገልግሎት እንዳይሰጥ የተደቀነበትን ፈተና እርሱና ዘመናዊ የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች እንዴት ሊቋቋሙትም ሆነ ሊታገሉት ይችላሉ?ANN JELLEMA----

«ከሚያደፋፍሩትም ሆነ ከሚያጽናኑት ሂደቶች አንዱ (በዚህ ዓመት ካደረግነው የኢንተርኔት ድራችን ጥናት ማለት ነው)፤ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አጠቃቀምና (WWW) የአንተርኔት መረጃ ድር ለችግሮች መፍትኄ በመሻት ረገድ መረባረባቸው ፤ የመገናኛ አገልግሎት እንዲሻሻል ማድረጋቸውና አወንታዊ ለውጥ ማምጣታቸው ነው። በዓለም ዙሪያ ለውጥ በመካሄድ ላይ ነው። በ 81 አገሮች ባደረግነው 80 ከመቶ ፍተሻ WWW እና ማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ፣ ህዝብ፣ ለለውጥ እንዲሣሣ በመቀስቀስ ዐቢይ ድርሻ ማበርከታቸውን ለመገንዘብ ችለናል።»

የኢንተርኔቱ የመረጃ ድር ፣ (Web) ከተፈለሰፈ ከ 23 ዓመት ወዲህ በዓለም አቀፍ ደረጃ የመረጃው ልውውጥ እጅግ በተፋጠነ ሁኔታ ነው የተስፋፋው። የኢንተርነቱ ድር በተፋጠነ ሁኔታ የዓለምን ህዝብ ማቀራረቡ እሙን ነው። ይሁንና በ «ኦንላይን» ላይ በሚደረገው ስለላና መሠረታዊ ዕውቀት ማስፋፊያ መረጃዎችን በማገድ፣ ዴሞካራሲ የቱን ያህል ይሆን አደጋ የተደቀነበት!?

Symbolbild - Landgericht Köln untersagt Volumen-Drosselung der Telekom
ምስል Fotolia/Calado

«እንደምንገነዘበው፣ ይኸው የአንተርኔት የመረጃ ድር ፣ ለ 21ኛው ክፍለ ዘመን የዴሞክራሲ ዕጣ ወሳኝ ድርሻ አለው ለፖለቲካ ክርክር ፣ ከጊዜ ወደ ጊዜ ዋና መድረክ በመሆን አገልግሎት በመስጠት ላይ ነው። በማደራጀቱም ረገድ ሚናው የሚናቅ አይደለም ስለዚህ፣ ሰዎች ይህን ነጻነታቸውን ተግባራዊ ካደረጉ ወይም ከበስተጀርባቸው የሚሠሩትን የሚሰልል ሊኖር ይችላል ብለው የሚያስቡት እውነት ከሆነ ዴሞክራሲ ተከለከለ ማለት ነው።

በተባበሩት መንግሥታት አጠቃላይ ጉባዔ ውይይት እንዲደረግበት ጀርመንና ብራዚል ያቀረቡት ሐሳብ በጣም ጠቃሚ ነው ብለን እናስባለን ምክንያቱም የግለሰብ የነጻነት መብት በኢንተርኔት ድር አገልግሎት «ኦንላይንም» ሆነ ከዚያ ውጭ («ኦፍላይን») እኩል መጠበቅ ይኖርበታል።»

በአዳጊ አገሮች የኢንተርኔቱን የመረጃ ድር በአግባቡ መጠቀም ምን ያህል እመርታ እንደሚያስገኝ የፊሊፒንስ አሠራር አርአያነት ያለው መሆኑን አን ጀሌማ አስረድተዋል። ፊሊፒናውያን ነጻና ግልጽ በሆነ መልኩ መረጃ ለመለዋወጥ፣ ትምህርትና ጤና አጠባበቅን ለማስፋፋት ነው የሚጠቀሙበት ፤ በአፍሪቃም ታዲያ ያ ዓይነቱ ተግባር የሚጠቅም መሆኑን አን ጀሌማ አብራርተዋል። ኢትዮጵያንና የኢንተርኔት መረጃ ድርን አጠቃቀም በማያያዝም እንዲህ ነበረ ያሉት--

«ኢትዮጵያ፤ የኢንተርኔት መረጃ ድርን ቅድመ ምርመራና ስለላን በተመለከተ በመዘርዝር ጥናታችን ውጤት መሠረት እጅጉን መጥፎ ውጤት ካገኙት አገሮች መካከል አንዷ ናት።

ከባድ ጉዳይ ነው በማለት መረጃዎች ለህዝብ እንዳይቀርቡ የሚያግዱአገሮች አሉ። ከማይፈለጉ የኤሌክትሮኒክስ መገናኛዎች ራስን መከላከል በሚል ፈሊጥ ይህን የሚገቱም አሉ። ኢትዮጵያ በሁለቱም ረገድ መጥፎ ውጤት ነው ያገኘች።»

ሰዎች፣ ነጻ የ«ኦንላይን» አገልግሎት እንዲያገኙ ለኢንተርኔት የመረጃ ድር ችግር የስነ ቴክኒክም ሆነ ሌላ ዓይነት መፍትኄ አልተገኘ ይሆን!? አያሌ መንግሥታት ባቻ ሳይሆኑ አንዳንድ ታላላቅ ኩባንያዎችም በኢንተርኔት አገልግሎት ረገድ ያላቸው ኃይል የሚበጅ እንዳልሆነ የገለጹት የ WWW ድርጅት ዋና ጉዳይ ፈጻሚ አን ጀሌማ እንዲህ አጠቃለዋል።

Internet in Entwicklungsländern
ምስል imago stock&people

«እንደሚመስለኝ፤ መፍትኄው በፖለቲካና በሥነ ቴክኒክ ፣ በሁለቱም እርምጃዎች በኩል ነው የሚገኘው። በመሠረቱ ዜጎች፤ የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች፤ መብታቸው እንዲከበር መጣር ይኖርባቸዋል። በ «ኦንላይን» የመጠቀም መብታቸው ከዚያ ውጭ እንዳለው የመብት ይዞታቸው እኩል የሚታይ ነው። እናም የፖለቲካ የለውጥ ሂደት ከሌለ፣ የሥነ ቴክኒክ መላም ካልተገኘ ውጤቱ የሚሠምር አይሆንም።»

ተክሌ የኋላ

ኂሩት መለሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ