1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢንተርኔት አፈና ተባብሷል-ፍሪደም ሃውስ

ሰኞ፣ ጥቅምት 22 2008

ፍሪደም ሃውስ የተባለው የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅት በዓለማችን ላይ የኢንተርኔት አፈና እየጨመረ መሄዱን በ2015ቱ የኢንተርኔት ነጻነት ሪፖርቱ ላይ ገለጸ። ድርጅቱ በጥናቱ ካካተታቸው 65 ሃገራት መካከል 32ቱ የኢንተርኔት ሳንሱርና አፈናን አጠናክረዋል ብሏል።

https://p.dw.com/p/1GxDV
Logo Freedom House

[No title]


የኢንተርኔት መረጃዎችን በይዘታቸው አማካኝነት ማፈን፣ ሰዎችን እርስ በርስ በተለዋወጧቸው መረጃዎች ምክንያት ማሰርና የኢንተርኔት መረጃዎች የሚሰልሉ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም መንግስታት የዜጎቻቸውን የኢንተርኔት ነጻነት እያፈኑ ነው መሆናቸዉን ድርጅቱ ገልጾአል። ግንባር ቀደም የኢንተርኔት አፋኞች ናቸው ካላቸው ሃገራት መካከል ደግሞ ቻይና፣ሶሪያ፣ኢራን፣ኢትዮጵያና ኩባ የገኙበታል። አይስላንድ፣ኢስቶኒያ፣ካናድ፣ጀርመንና አወስትራሊያ የኢንተርኔት ነጻነት ከተረጋገጠባቸው ሀገራት ቀዳሚዎቹ ናቸው። 2.9% ለሆነው ህዝቧ ብቻ የኢንተርኔት አገልግሎት እያቀረበች ያለችው ኢትዮጵያ የማህበራዊ ድረ-ገጾችን ታግዳለች፣የፖለቲካና ማህበራዊ ጉዳዮች ይዘት ያላቸውን መረጃዎች ታፍነለች፣ የኢንተርኔት ጸሀፍትንና የኮምፒዉተርና ኤሌክትሮኒክስ ተጠቃሚዎችን ታስራለች ሲል ፍሪደም ሀውስ በሪፖርቱ ከሷል። የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን ናትናኤል ወልዴ ተጨማሪ ዘገባ ልኮልናል።


ናትናኤል ወልዴ

አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ