1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«የኢኖቬሽን» የፈጠራ ሳምንት

ዓርብ፣ ሰኔ 7 2011

በኢትዮጵያ ለአንድ ሳምንት የተካሄደው የኢኖቬሽን ወይም የፈጠራ ሳምንት ዛሬ በአፍሪቃ አዳራሽ በተካሄደ ስነ ስርዓት ተጠናቋል። አላማውም ኢትዮጵያን ለመጪው ዘመን ማስተዋወቅ መሆኑን አቶ ሲሳይ ቶላ የቴክኖሎጂ እና የፈጠራ ሚኒስትር ዴታ ለዶቼቬለ «DW» ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/3KINk
Äthiopien - Staatsminister für Innovation und Technologie
ምስል DW/Y. Geberegziabher

የፈጠራ ሳምንት

ኢትዮጵያ በዲጂታል የኢኖቬሽን ወይም የፈጠራ ዘርፍ ራስዋን ለማስተዋወቅና ልምድ ለመቅሰም ያለመ የተባለለት የኢኖቬሽን ወይም የፈጠራ ሳምንት ተካሂዶአል። ዛሬ የተጠናቀቀዉን ዝግጅት ያሰናዳዉ የፌደራል ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር መሆኑን ሚኒስትር ዴታዉ አቶ ሲሳይ ቶላ ለዶይቼ ቬለ «DW» ተናግረዋል። ፕሮግራሙ ሦስት አይነት መድረኮችን ያካተተ ነበር።  በመጀመርያዉ በሚሊኒየም አዳራሽ የተከናወነዉ የ ICT ዓዉደ ርዕይ ነዉ። ሁለተኛዉ ዓዉደርዕይ የፈጠራ ስራ ጀማሪዎች መድረክ ሲሆን ሦስተኛዉ ከአፍሪቃ እና ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ታላላቅ ኩባንያዎች የተሳተፉ በት «ኢኖቬሽን አፍሪቃ ዲጂታል ሰብሚት» በሚል የተከናወኑ መሆናቸዉ ታዉቋል። በ «ICT» ቴክኖሎጂ በዓለማችን በተለይ ኢኮኖሚዉን ከማንቀሳቀስ አንጻር የተደረሰበት ደረጃ የተዳሰሰ ሲሆን የቴክኖሎጂዉ ተግዳሮቶች በተለይ ለአፍሪቃ ብሎም ለኢትዮጵያ የሚሉ ዝርዝር ጉዳዮች ታይተዋል። ያደጉ አገሮች በመስኩ ያላቸዉ ልምድ አዳጊዎቹ ሃገራት ላይ ብልጫ « ጥቅም» ሊወስዱባቸዉ እንደሚችሉ የቴክኖሎጂዉ መሠረተ ልማት አለመስፋፋት ሕጋዊ ማዕቀፍ አለመኖር እንደተግዳሮቶች ተጠቅሰዋል። በዝግጅቱ ላይ የተለያዩ የፈጠራ ሥራዎችን ላቀረቡ ሽልማት ተሰጥቶአል።  

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 
አዜብ ታደሰ