1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ተቃውሞው ቀጥሏል

ረቡዕ፣ ሐምሌ 19 2009

እስራኤል በብረት መለያ መሳሪያ ለመፈተሽተተክሎ የነበረዉን መሳሪያ ትናንት አንስቷል።ይሁንና ምዕመናንን የሚቆጣጠርበት የቪዲዮ ካሜራ ግን አሁንም እንዳለ ነዉ።

https://p.dw.com/p/2hC15
Jerusalem Ausschreitungen an der Al-Aqsa Moschee
ምስል picture alliance/dpa/AA/M. Alkharouf

የኢየሩሳሌሙ ግጭት


የእስራኤል መንግስት እየሩሳሌም ወደ ሚገኘዉ የሙስሊሞች ቅዱስ መስጊድ አል አቅሳ ለሶላት የሚገቡ ሰዎችን  በብረት መለያ መሳሪያ ለመፈተሽ ተክሎት የነበረዉን መሳሪያ ትናንት አንስቷል።ይሁንና ምዕመናንን የሚቆጣጠርበት የቪዲዮ ካሜራ ግን አሁንም እንዳለ ነዉ።በዚሕም ምክርንያ መፈተሻዉ መሳሪያ ከተተከለ ጀምሮ ፍልስጤሞች የሚያደርጉት ተቃዉሞ ዛሬም እንደቀጠለ ነዉ።ተቃዉሞና ግጭቱ እንዳይጠናከር እና ወደ ሌላ ሥፍራ እንዳይዛመት የተለያዩ መንግሥታት እና ማሕበራት የሚያደርጉት ጥሪም እንደቀጠለ ነዉ።

ዜናነህ መኮንን

ነጋሽ መሐመድ