1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢድ አልፊጢር በአል በአዲስ አበባ

ሰኞ፣ መስከረም 3 2003

የኢድ አልፊጥር በአል ለ1431ኛ ጊዜ በመላዉ አለም በድምቀት እየተከበረ ነዉ።

https://p.dw.com/p/P9Av
ምስል AP

ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ደግሞ በአሉን በዘመን መለወጫ በአል-ዝግጅት ጭምር ነዉ-ያከበሩት።ከአዲስ አበባ እንጀምር። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ታደሠ እንግዳዉ የርዕሠ-ከተማይቱ የበአል-አከባበር ተከታትሎት ነበር።

BdT Moschee in Indie Neu Delhi
ምስል AP

መቀሌ-ትግራይ፤ ወኪላችን ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር እንደተመለከተዉ በአሉ በተለይ ጎደና ሰማዕታት ተብሎ በተሰየመዉ አዲስ አዉራ ጎዳና ላይ በተደረገ የአል-መሻድ ስገት ነበር የተጀመረዉ።

የአስመራዉ ወኪላችን ጎይቶም ቢሆን እንደተከታተለዉ የኤርትራ በተለይ ደግሞ የአስመራ አዉራ መንገዶች በበዓለተኛዉ ተጨናንቀዉ ነዉ-ነበር ያረፈዱት።

ቀይ ባሕር ማዶ ሳዑዲ አረቢያ በተለይም በሙስሊሞቹ ቅዱስ ስፍራዎች መካሕ እና መዲና ዉስጥ በተደረገዉ የአል-መሻድ ስግደት ከ2.5 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ተካፍሏል። የጂዳዉ ወኪላችን ነብዩ ሲራክ እንደታዘበዉ ሳዑዲ አረቢያ የሚኖሩ በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን ኢድ አልፊጥርን ያዉ እንደበአል በደስታ ቢያከብሩም-የበአል ደስታቸዉ በታሰሩ ወገን-ዘመዶቻቸዉ ስቃይ እሁለት የተከፈለ ነበር።

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ