1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢድ አል አድሀ አከባበር በአዲስ አበባ ስታድዮም

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 15 2010

የኢድ አል አድሀ በዓል በኢትዮጵያ በተለይም በአዲስ አበባ ስታድዮም በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በስግደት እና የፀሎት ስነስርዓት ዛሬ ጠዋት ተከብሯል። በበዓሉ ላይ የተገኙት የሃይማኖት መሪዎች እና የከተማዋ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በስነ ስርዓቱ ላይ ባሰሙት ንግግር የሰላም የአንድነት እና የመረዳዳት መልዕክቶች እና ጥሪዎችን አስተላልፈዋል።

https://p.dw.com/p/33WI3
Äthiopien Eid al Adha Fest in Addis Abeba
ምስል DW/G. Tedla

የአረፋ አከባበር በአዲስ አበባ

ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ሙስሊሞች ዛሬ የኢድ አል አድሀ አረፋ በዓል እየተከበረ ነው። በዓሉ በኢትዮጵያ በተለይም በአዲስ አበባ ስታድዮም በርካታ የእምነቱ ተከታዮች በተገኙበት በስግደት እና የፀሎት ስነስርዓት ዛሬ ጠዋት ተከብሯል። በበዓሉ ላይ የተገኙት የሃይማኖት መሪዎች እና የከተማዋ ከፍተኛ ባለሥልጣናት በስነ ስርዓቱ ላይ ባሰሙት ንግግር የሰላም የአንድነት እና የመረዳዳት መልዕክቶች እና ጥሪዎችን አስተላልፈዋል። ስነ ስርዓቱን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ 
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ