1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢድ አል ፈጥር በዓል አከባበር

ሐሙስ፣ ነሐሴ 2 2005

1434ኛው የእድ አል ፈጥር በዓለ ዛሬ በሙሥሊም ሀገራት ተከበረ። ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆኑ የሙሥሊሙ ህብረተሰብ አባላት በአዲስ አበባ ስቴድየም የተካሄደውን የበዓሉን አከባበር ሥነ ሥርዓት ወደዚያ በመሄድ እና በዙርያው በመገኘት ተከታትለውታል።

https://p.dw.com/p/19MSn
2013 Eid Al-Fatir at Addis Abeba Stadium in Äthiopien. Autor: Getachew Tedla HG, DW-Korrespondent
ምስል DW

 በዚሁ ወቅትም ብዙዎች ከስቴድየም ውጭ ተቃውሞአቸውን በከፍተኛ ድምፅ ያሰሙ እንደነበር እና በሌሎች አካባቢዎችም ከበዓሉ በኋላ  በምዕመናኑ እና በፀጥታ አሰከባሪዎች መካከል ከፍተኛ ግጭት እንደታየ ከአዲስ አበባ የደረሰን ዘገባ አመልክቶዋል።

ሌላው ወኪላችን ዮሀንስ ገብረእግዚአብሄር በስቴድየም በኩል አድርጎ መርካቶ ወደሚገኘው አንዋር መስጊድ እና ፒያሳ ወደላው የቤኒን መስጊድ በመሄድ ስለ በዓሉ አከባበር እና ተቃውሞ  ስለመኖር አለመኖሩ  ለማየት ሞክሮ ነበር። በነዚህ ስፍራዎች ስላየው ሸዋዬ ለገሰ በስልክ ጠይቃው ነበር።

ጌታቸው ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሄር

አርያም ተክሌ

ሸዋዬ ለገሠ