1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የ«ኢጋድ»እና የ«ኤስ ፒ ኤል ኤም» ውይይት

ማክሰኞ፣ ግንቦት 5 2006

ለደቡብ ሱዳን ውዝግብ መፍትሔ የማፈላለጉ ጥረት ከእስር የተፈቱት 11 የመንግሥቱ የቀድሞ ባለሥልጣናትም የአጠቃላዩ የሰላም ድርድርሩ አባል መሆን እንዳለባቸው በመታመኑ ተቀናቃኝ ወገኖችን ለማስታረቅ የሽምግልና ጥረት ከጀመረው የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት ባለሥልጣን ፣ ኢጋድ ተወካዮች ጋ ዛሬ በአዲስ አበባ ውይይት ጀመሩ።

https://p.dw.com/p/1Bz4p
ምስል DW

11ዱ የደቡብ ሱዳን ሕዝብ ነፃ አውጪ ንቅናቄ፣ «ኤስ ፒ ኤል ኤም » አመራር አባላት ፣ ካለፈው ታህሳስ ወር ወዲህ በፕሬዚደንት ሳልቫ ኪር መንግሥት ጦር እና በቀድሞው ምክትላቸው ሪየክ ማቸር ሚሊሺያዎች መካከል ፣ ምንም እንኳን መሪዎቹ ሰሞኑን የተኩስ አቁም ስምምነት ቢፈርሙም አሁንም በቀጠለው ውጊያ ላይ እጃቸው እንዳለበት አደራዳሪው አምባሳደር መሥፍን በመግለጽ ፣ እነሱ የሚሰጡት ሀሳብ ለአጠቃላዩ የሰላም ድርድር አስተዋፅዖ እንደሚኖረው አስረድተዋል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

አርያም ተክሌ

ነጋሽ መሀመድ