1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢጣሊያ ርምጃና አዉሮጳ ፍርድ ቤት ብይን

ዓርብ፣ የካቲት 16 2004

ወደ ሊቢያ ከተመለሱት ስደተኞች አስራ-ሰወስት የኤርትራና አስራ-አንድ የሶማሊ ዜጎች በአንድ የስደተኞች መብት ተሟጋች ድርጅት አማካይነት የኢጣሊያን መንግሥት ከሰዉ ሲከራከሩ ነበር።ትናንት ሽትራስቡርግ-ፈረንሳይ ያስቻለዉ ፍርድ ቤት ኢጣሊያ ለያንዳዱ ስደተኛ አስራ-አምስት ሺሕ ዩሮ ካሳ እንድትሰጥ---

https://p.dw.com/p/149s0
Migrants receives assistance as they arrive on the tiny island of Lampedusa, Italy, early Sunday, May 8, 2011. Italian police and coast guard officials on Sunday rescued some 400 illegal migrants coming from Libya whose boat was tossed against rocks near port in southern Italy after the steering malfunctioned, officials said. Tens of thousands of migrants have fled unrest in northern Africa since January, most arriving at Lampedusa, the nearest Italian port to Africa. (AP Photo/Francesco Malavolta)
ስደተኞች-ላምፔዱሳምስል AP

የኢጣሊያ መንግሥት ወደ ሐገሩ ለመግባት የሞከሩ የሶማሊያና የኤርትራ ስደተኞችን አስገድዶ ወደ ሊቢያ በመመለሱ ካሳ እንዲከፍል የአዉሮጳ የሰብአዊ ጉዳይ ፍርድ ቤት በየነበት።የኢጣሊያ ጠረፍ ጠባቂ ወታደሮች እንደ ጎሮጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር በ2009 በመርከብ ወደ ኢጣሊያ ለመግባት የሞከሩ አፍሪቃዉያን ስደተኞችን አስገድደዉ ወደ ሊቢያ መልሰዋቸዉ ነበር።ወደ ሊቢያ ከተመለሱት ስደተኞች አስራ-ሰወስት የኤርትራና አስራ-አንድ የሶማሊ ዜጎች በአንድ የስደተኞች መብት ተሟጋች ድርጅት አማካይነት የኢጣሊያን መንግሥት ከሰዉ ሲከራከሩ ነበር።ትናንት ሽትራስቡርግ-ፈረንሳይ ያስቻለዉ ፍርድ ቤት ኢጣሊያ ለያንዳዱ ስደተኛ አስራ-አምስት ሺሕ ዩሮ ካሳ እንድትሰጥና የከሳሾችን ወጪ በሙሉ እንድትሸፍን በይኗል።የሮማ ወኪላችን ተኽለ እግዚ ገብረ እየሱስ ዝር ዝር ዘገባ ልኮልናል።

ተኽለ እግዚ ገብረ እየሱስ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

የአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት ኢጣልያ የሰብዓዊ መብት ጥሳለች ሲል ውሳኔ አሳለፈ ። ፍርድ ቤቱ ያሬ ባሳለፈው ውሳኔ ኢጣልያ ከ 2 ዓመት በፊት በሜዴትራኒያን ባህር አቋርጠው ወደ ኢጣልያ በማቅናት ላይ የነበሩ አፍሪቃውያን ስደተኞች ወደ ሊቢያ በማባረር ሰብዓዊ መብታቸው ጥሳለች ሲል አስታውቋል ። በወቅቱ 24 የሶማሊያ የኤርትራ ስደተኞች ወደ ኢጣልያዋ የወደብ ከተማ ላምፔዱዛ በመጠጋት ላይ ሳሉ ነበር ኢጣልያ እ.ጎ.አ በ 2008 ዓም ከሟቹ የሊቢያ መሪ ኮሎኔል ከሞአመር ጋዳፊ ጋር በደረሰችው ስምምነት መሠረት እንዲባረሩ ያደረገችው ። ፍርድ ቤቱ እንዳለው ኢጣልያ ስደተኞቹን በመባረር እ.ጎ.አ በ 1951 የፀደቀውን የጄኔቫው ስምምነት በተለይም የስደተኞችን አያያዝ የሚመለከተውን አንቀፅ 3 ን ጥሳለች ። በተጨማሪም ስደተኞቹን ወደ ሶማሊያ እና ኤርትራ ለመወሰድ አደጋ አጋልጣቸውም ነበር ሲል ፍርድ ቤቱ በሙሉ ድምፅ ተስማምቷል ። ኢጣልያ ከ 2 ዓመት በፊት ወደ ኢጣልያ የባህር ክልል ለመሻገር የሚሞክሩ ስደተኞችን ወደ ተነሱበት ቦታ እንድትመልስ ከጋዳፊ ጋር የፈረመችው ስምምነት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ና በካቶሊክ አብያተ ክርስቲያን ተወግዟል ።

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ