1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤሊዜ ውል 50 ኛ ዓመት

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 3 2004

ለፈረንሳይ ጀርመን የጠበቀ ግንኙነት መሰረት የጣለው የእርቅ ውል 50ኛ ዓመት ባለፈው እሁድ ፈረንሳይ ውስጥ በተካሄደ ስነስርዓት ታስቧል ። የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክልና የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ፍራንሷ ኦሎንድ በተገኙበት

https://p.dw.com/p/15Uim
German Chancellor Konrad Adenauer, left, hugs France President Charles de Gaulle, right, after signing the Elysee friendship treaty in the Elysee palace in Paris, France on Jan. 22, 1963. France and Germany kicked off celebrations Wednesday, Jan. 22, 2003 to mark the 40th anniversary of the treaty with a raft of events intended to inject new vitality into their relationship, which is pivotal in efforts to expand and integrate the European Union. (ddp images/AP Photo) --- Bundeskanzler Konrad Adenauer (li) und Staatspraesident Charles de Gaulle umarmen sich nach der Unterzeichnung des Deutsch-Franzoesischen Vertrages am 22. Januar 1963 im Salon Murat im Pariser Elysee-Palast. Rechts neben de Gaulle steht M. Christian Fouchet. (ddp images/AP Photo)
ምስል AP

በዚሁ ስነ ስርዓት ላይ ለፈረንሳይ ጀርመን የጠበቀ ግንኙነት መሰረት የጣለው የእርቅ ውል 50ኛ ዓመት ባለፈው እሁድ ፈረንሳይ ውስጥ በተካሄደ ስነስርዓት ታስቧል ። የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክልና የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ፍራንሷ ኦሎንድ በተገኙበት በዚሁ ስነ ስርዓት ላይ ውሉን የፈረሙት የዚያን ጊዜዎቹ የሁለቱ አገራት መሪዎች ተወድሰዋል ። የአውሮፓ ህብረት መሰረት የሆኑት ሁለቱ አገሮች ህብረቱ ያጋጠመውን የገንዘብ ቀውስ ለመፍታት በየጊዜው የሚያጋጥሙ ልዩነቶቻቸውን እያጠበቡ በጋራ በመንቀሳቀስ ላይ ናቸው ። የጀርመንና የፈረንሳይ ግንኙነት የእርቅ ውልና አስተምህሮቱ የዛሬው አውሮፓና ጀርመን ዝግጅታችን ትኩረት ነው ።

epa03300185 French President Francois Hollande (R) and German Chancellor Angela Merkel (L) listen to the national anthems during a ceremony to commemorate the 50th anniversary of the official Franco-German reconciliation, in Reims, France, 08 July 2012. German Chancellor Angela Merkel and French President Francois Hollande met 08 July in the French town of Rheims, to commemorate their countries' postwar reconciliation. The two leaders attended a memorial service at Rheims Cathedral, marking the 50th anniversary of the 08 July 1962 meeting in the town of France's Charles de Gaulle and Germany's Konrad Adenauer - who signed a Franco-German friendship treaty. EPA/YOAN VALAT
ምስል picture-alliance/dpa
Schüler einer deutsch-französischen Schulklasse winken am Donnerstag (23.01.2003) dem französischen Staatspräsidenten Jacques Chirac und Bundeskanzler Gerhard Schröder vor der Konrad-Adenauer-Stiftung in Berlin mit Fähnchen zu. Fotograf: Michael Hanschke dpa/lbn
ምስል picture-alliance/dpa


ኃያላኑ የአውሮፓ ሃገራት ጀርመን ና ፈረንሳይ እንዲህ እንደ አሁኑ ጥብቅ ወዳጅ ሳይሆኑ ወደ 100 ዓመት ለሚጠጋ ዘመን በጠላትነት የሚተያዩ ባላጋራዎች ነበሩ ። ሁለቱ ሃገራት ለዘመናት ሆድና ጀርባ ሆነው የቆዩትም በተለያዩ ጊዜያት ባካሄዷቸው ጦርነቶች ምክንያት ነው ። ለበርካታ ዓመታት ጀርመን የኖሩትና የተማሩት የታሪክ ምሁር ዶክተር ልጅ አስፋወሰን አሥራተ ካሳ የሁለቱን አገሮች ጥላቻ ከመነሻው ይዘረዝራሉሁለተኛው የዓለም ጦርነት በናዚ ጀርመን ሽንፈት ከተደመደመ ከ 18 ዓመታት በኋላ ነበር የጀርመንና የፈረንሳይን ግንኙነት ታሪክ ለመቀየር የበቃው ስምምነት ላይ የተደረሰው ። እጎአ ሐምሌ 8 1962 ዓም ፓሬስ ፈረንሳይ ውስጥ የዚያን ጊዜው የጀርመን መራሄ መንግሥት ኮናርድ አደናወርና የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ሻርል ደጎል የኤሊዜ ውል የሚል ስያሜ የተሰጠውን ስምምነት ፈረሙ ። ለሁለቱ አገራት ግንኙነት ስምረት መሰረት የጣለው ይኽው ውል ሊፈረም የቻለው በመሪዎቹ ጥንካሬና እምነት መሆኑን ዶክተር ልጅ አስፋወሰን ያስረዳሉ ።

። ሁለቱ ባለራዕይ መሪዎች በፈረሙት ውል መሰረት የመንግሥታቱ ተወካዮች የውጭ ደህንነትን የወጣቶችንና የባህል ግንኙነቶችን በመሳሰሉ ጠቃሚ ጉዳዮች ላይ በየጊዜው ምክክሮች ማካሄድ ጀመሩ ። ኮናርድ አደናውርና ሻርል ደጎል በሁለቱ አገራት ወጣቶች መካከል መተማመን እንዲሰፍን የሰጡት ትኩረት ሁለቱ የቀደሞ ባጋራዎች በአውሮፓ ወሳኝ ሚና ያላቸው ወዳጆች የሆኑበትን መንገድ ጠረገ በሂደትም ታሬካዊው የኤሊዜ ውል የመንግሥታቱንና ህዝቦችን ግንኙነት በእጅጉ ቀየረ ። ከ40 ዓመታት በላይ ጀርመን የኖሩት ዶክተር ልጅ አስፋወሰን ወሉ ያስከተለውን ለውጥ የታዘቡ የዓይን ምስክር ናቸው ። ከትናንት በሰተያ እሁድ 50 ዓመት የደፈነው የኤሊዜ ውል ከምንም በላይ ለአውሮፓ አንድንት መጠናከር ያደረገው አስተዋፅኦ የጎላ መሆኑ ይወሳል ። የ2ቱ አገሮች ወዳጅነት የህብረቱ መሰረት ሲሆን በዚህ ሂደትም የአሁኖቹም ሆኑ የቀደሙት መሪዎች ሚና ትልቅ ድርሻ አለው እንደ ዶክተር ልጅ አስፋወሰን
የጠላትነትን ጠባሳ ሽሮ ጥብቅ ወዳጅነትን ያሰፈነው የጀርመንና የፈረንሳይ የእርቅ ውል ለ ሌሎች የአውሮፓ ሃገራት በአርያነት ሊወሰድ የሚችል እንደሆነ ይታመናል ።
የጀርመንና የፈረንሳይ የእርቅ ውል 50 ኛ ዓመት ሲታሰብ ከዚያ አስቀድሞ ኢትዮጵያ ተመሳሳይ እርምጃ በመውሰድ በታሪክ ቀዳሚዋ ሃገር መሆኗ ሊዘነጋ አይገባም ይላሉ ዶክተር አስፋወሰን አሥራተ ካሳ ።


የጦርነት ጠባሳ ሽሮ ወዳጅነት እንዲሰፍን መሰረት የጣለው የጀርመንና የፈረንሳይ ውል 50ኛ ዓመት በአንደኛው የዓለም ጦርነት በጀርመን የቦምብ ድብደባ ከባድ ጉዳት በደረሰበት ራይም በተባለው የፈረንሳይ ከተማ ውስጥ በሚገኝ ካቴድራል ባለፈው እሁድ በደመቀ ስነ ስርዓት ታስቧል ። በዋዜማው ደግሞ እዚያው ከተማ ውስጥ በ1ኛው የዓለም ጦርነት የተገደሉ የጀርመን ወታደሮች መካነ መቃብር መደፈሩ ጥላቻው እስካሁን ሙሉ በሙሉ መሻሩን አጠያያቂ ሊደርገው ይችላል ። እንደ ዶክተር አስፋ ወሰን ግን በአሁኑ ሰዓት ይህን መሰሉ አስተሳሰብ ያላቸው ዜጎች ጥቂት ናቸው ።
የጀርመንና የፈረንሳይና ግንኙነት የለወጠው የኤሊዜ ውል ላይ ያተኮረው የዛሬው አውሮፓና ጀርመን ዝግጅታችን በዚሁ አበቅቷል ። በዝግጅቱ ማብራሪያ በመስጠት የተባበሩኝን ዶክተር ልጅ አስፋወስን አሥራተ ካሳን እያመሰገንኩ በዚሁ የምለያችሁ ሂሩት መለሰ ነኝ ።

Der französische Staatspräsident Charles de Gaulle (r) und der deutsche Bundeskanzler Konrad Adenauer unterzeichnen am 22.1.1963 im Pariser Elysee-Palast den deutsch-französischen Freundschaftsvertrag. Deutschland und Frankreich wollen mit einer feierlichen politischen Erklärung am 22. Januar 2003 40 Jahre deutsch-französische Freundschaft und Zusammenarbeit würdigen. Das als Elysée-Vertrag in die Geschichte eingegangene Abkommen über die deutsch-französische Zusammenarbeit hat die Nachbarn nach langer "Erbfeindschaft" und blutigen Kriegen seit 1963 immer mehr zusammengeführt. In dem Vertrag verpflichten sich beide Regierungen zu Konsultation in allen wesentlichen Fragen der Außen-, Sicherheits-, Jugend- und Kulturpolitik. Beide Seiten setzten Koordinatoren für die deutsch- französische Zusammenarbeit sowie Bevollmächtigte für kulturelle Angelegenheiten ein.
ምስል picture-alliance/dpa

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሰ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ