1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤሌትሪክ ኃይል መቆራረጥ ችግር በአዋሳ 

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 22 2011

በሀዋሳ ከተማ በተደጋጋሚ በሚከሰተው የኤሌትሪክ ኃይል መቆራረጥ በስራችን ላይ ችግር እያስከተለብን ነው ሲሉ ነዋሪዎች አማረሩ። የኃይል መቆራረጡ ምክንያት የመስመሮች እርጅና ነው ያለዉ የደቡብ ክልል ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ጽ/ቤት በበኩሉ መስመሮችን በአዲስ የመተካት ስራ በማከናውን ላይ እንደሚገኝ ተናግሮአል።

https://p.dw.com/p/3HhXX
Glühbirne in Simbabwe
ምስል DW

ያረጁት የኤሌትሪክ መስመሮች እየቀየሩ ነዉ

በሀዋሳ ከተማ በተደጋጋሚ በሚከሰተው የኤሌትሪክ ኃይል መቆራረጥ በስራችን ላይ ችግር እያስከተለብን ነው ሲሉ ነዋሪዎች አማረሩ። በኤሌትሪክ ኃይል መቆራረጥ ሳቢያ የድርጅቶቻቸውን ሰራተኞች ለመቀነስ ከመገደዳቸውም በላይ የብድር ዕዳቸውን ለመክፈል መቸገራቸውን ተናግረዋል።  የኃይል መቆራረጡ ምክንያት የመስመሮች እርጅና ነው የሚለው የደቡብ ክልል ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ጽ/ቤት በበኩሉ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ነባር የኃይል መስመሮችን በአዲስ የመተካት ስራ በማከናውን ላይ እንደሚገኝ ይናገራል።  የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች እንደሚሉት በከተማው በተደጋጋሚ የሚከሰተው የኤሌትሪክ ኃይል መቆራረጥ በስራቸው ላይ ተድኖ እያሳደረባቸው ይገኛል።  በከተማው አረብ ሰፈር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደጉር ስራ እተዳደራለሁ የምትለው ወጣት ሀብታም ዳና ያለምንም ቅድመ ማስጠንቀቂያ በድንገት በሚከሰተው የኃይል መቆራረጥ መደበኛ ስራዋን ማከናወን አንዳልቻለች ተናግራለች። 
ከባንክ ባገኙት የገንዘብ ብድር በማህበር ተደራጅተው በብረታ ብረት ስራ ተሰማረተው እንደሚገኙ የጠቀሰው ሌላው አስተያየት ሰጪ በበኩሉ ይሁንእንጂ በኃይል መቆራረጥ ሳቢያ የማህበሩን ሰራተኞች ለመቀነስ ከመገደዳቸውም በላይ የብድር ዕዳቸውን ለመክፈል መቸገራቸውን ገልዶል። ዶቼ ቪለ «DW» በነዋሪዎቹ ቅሬታ ዙሪያ ያነጋገራቸው የደቡብ ክልል ኢሊክትሪክ ኃይል አገልግሎት  ጽ/ቤት የስራ ሃላፊዎች ነዋሪዎቹ ያቀረቡት ቅሬታ ትክክለኛ መሆኑን አረጋግጠዋል። የኃይል መቆራረጡ እየጋጠመ የሚገኘው አነስተኛ ኃይል ተሸካሚ መስመሮች በማርጀታቸው ምክንያት መሆኑን የጽ/ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ስራ አስኪያጅ አቶ ያቆብ ታሪኩ ገልደዋል። የሀዋሳ ከተማ በአገር አቀፍ ደረጃ የኤሌትሪክ ማሻሻያ ተግባራዊ እየተደረገባቸው ከሚገኙ ስምንት ከተሞች አንዶ መሆኑን የጠቆሙት ስራ አስኪያጁ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ነባር የኃይል መስመሮችን በአዲስ የመተካት ስራ በመከናወን ላይ የገኛሉ ብለዋል።


ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ 


አዜብ ታደሰ 
እሸቴ በቀለ