1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤሌክትሮኒክስ የርቀት ትምህርትና አፍሪቃ

ረቡዕ፣ ግንቦት 19 2001

የኤሌክትሮኒክስ የርቀት ትምህርት የወደፊቱ የአፍሪቃ የትምህርት አሰጣጥ ዘዴ መሆኑ እንደማይቀር የአንዳንዶች ዕምነት ነው ። በርካታ ችግሮች ባሉበት በዚህ ክፍለ ዓለም ለአንዳንዶች ደግሞ ይህ የህልም እንጀራ ነው የሚመስለው ።

https://p.dw.com/p/Hydr
አፍሪቃውያን ህፃናት በኮምፕዩተር ሲማሩምስል picture-alliance/dpa

የኤሌክትሮኒክስ መገናኛ ብዙሀን የማስተማር አቅም እስከ ምን ድረስ እንደሆነ ከዛሬ ጀምሮ ለሚቀጥሉት ሶሶት ቀናት ዳካር ሴኔጋል ውስጥ የሚካሄደው ጉባኤ 1500 ተሳታፊዎች ይወያያሉ ። በአፍሪቃ ትምህርትን በኢንተርኔት አማካይነት ለመከታተል ስላለው ዕድል ያን ሾልዝ የዘገበውን ሂሩት መለሰ አጠናቅራዋለች ።

ያን ሾልዝ / ሂሩት መለሰ /ተክሌ የኋላ