1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርትራና የጅቡቲ ውዝግብና የጸጥታ ጥበቃው ምክር ቤት ማሳሰቢያ

ቅዳሜ፣ መጋቢት 26 2001

ኤርትራ በጅቡቲ ግዛት አስገብታዋለች የተባለዉን ጦርዋን እንድታስወጣ የተመድ ጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ባለፈው ጥር ወር ያሳለፈውን ውሳኔ እንድታከብር የወቅቱ

https://p.dw.com/p/HSyW
ምስል AP Graphics/DW

የምክር ቤቱ ፕሬዚደንት የሜክሲኮ አምባሳደር ክሎድ ሄለር ትናንት በድጋሚ አሳሰቡ። ኤርትራ ለውዝግቡ መፍትሄ እንድትሻም አምባሰደሩ አክለው ጠይቀዋል። ይሁንና፡ ኤርትራ የጅቡቲን ግዛት በኃይል ይዛለች የተባለበት የጅቡቲ ክስ ከሀቅ የራቀ እና የኤርትራን ስም ለማጉደፍ ሆን ተብሎ የተደረገ ሤራ ነው ስትል አጣጥላዋለች። ጎይትኦም ቢሆን የኤርትራ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ ፍስሀጽዮን ጴጥሮስን አነጋግሮዋል።

ጎይቶም ቢሆን/አርያም ተከሌ

ነጋሽ መሐመድ