1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርትራውያን ስደተኞች መበራከት

ረቡዕ፣ ኅዳር 10 2007

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን ባለፈው ወር ብቻ ከ5000 በላይ ኤርትራውያን ድንበር ተሻግረው በኢትዮጵያ ጥገኝነት መጠየቃቸውን አስታወቀ።በኢትዮጵያ የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ቁጥር

https://p.dw.com/p/1Dq2c
Israel afrikanische Einwanderer im Haft bei Ketziot
ምስል picture-alliance/dpa

ከ107,000 በላይ ደርሷል። የህጻናት ስደተኞች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው።

ኢትዮጵያና ኤርትራ የግዛት ይገባኛል ጥያቄ በወለደው ጦርነት ከታመሱ በኃላ ግንኙነታቸው ሰላም ርቆት ዛሬ ድረስ ዘልቋል። ሁለቱ የምስራቅ አፍሪቃ ሃገራት የሚዋሰኑት የድንበር አካባቢም በጥብቅ ወታደራዊ ቁጥጥር ስር ነው። ይህ ግን በግዳጅ ወታደራዊ አገልግሎት የተማረሩትን እና የተሻለ የኑሮ ሁኔታ የሚፈልጉትን ኤርትራውያን አላገዳቸውም። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን የኢትዮጵያ ቢሮ ቃል-አቀባይ አቶ ክሡት ገ/እግዚአብሄር በአሁኑ ወቅት ከ5,000 በላይ ስደተኞች በየወሩ ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚገቡ ይናገራሉ።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን ባለፈው ወር ባወጣው ሪፖርት ከ110, 000 በላይ ስደተኞች በሱዳን እንደሚገኙ አስታውቋል። አቶ ክሱት ገ/እግዚአብሄር ወደ ኢትዮጵያ የሚሰደዱ ኤርትራውያን ቁጥር ከዚህ በላይ ሊጨምር እና በሱዳን ከሚገኙት ሊበልጥ ይችላል የሚል ስጋት አላቸው። ወደ ኢትዮጵያ ከሚሰደዱት መካከል ከ97 በመቶ በላይ የሚሆኑት እድሚያቸው ከ18-24 የሚገኝ ወጣቶች ናቸው። ለእነዚህ ስደተኞች እገዛ ለሚያደርገው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን ብቻቸውን የሚመጡ ህጻን ስደተኞች ጉዳይ አሳሳቢ እንደሆነበት አቶ ክሡት ገ/እግዚአብሄር ይናገራሉ።

የኤርትራውያን ስደተኞች ቁጥር እድገት በኢትዮጵያ እና ሱዳን ብቻ የተወሰነ አይደለም። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን ሪፖርት መሰረት እ... 2014 ብቻ ወደ 37,000 የሚጠጉ ኤርትራውያን በአውሮጳ ሃገራት ጥገኝነት ጠይቀዋል። ይህ ቁጥር ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር በ13,000 እንደሚልቅ የኮሚሽኑ መግለጫ ያትታል። በኢትዮጵያ እና ሱዳን ከሃገራቸው የሚወጡት ኤርትራውያን በስዊድን፣ጀርመንና ስዊዘርላንድ ተገን መጠየቃቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን ቃል-አቀባይ አድሪያን ኤድዋርድስ ተናግረዋል። በጀልባ ወደ አውሮጳ ከሚገቡ ስደተኞች መካከል 22 በመቶው ኤርትራውያን ናቸው። 34,000 ኤርትራውያን በጀልባ ጣልያን መድረሳቸውን የጠቆመው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽን ሪፖርት ይህም ከሶርያ ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ የሚጠቀስ ነው።

እሸቴ በቀለ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ