1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርትራውያን ስደተኞች ምስክርነት በኢጣልያ

ሐሙስ፣ ጥር 8 2006

ለፍርድ ቤት ቃላቸውን የሰጡት 7 ኤርትራውያን ስደተኞች ናቸው ። ከመካከላቸው በተከሳሹ የተደፈረች የ18 ዓመት ልጃገረድ ትገኝበታለች ።

https://p.dw.com/p/1AsNs
ምስል picture-alliance/ROPI

በህገ ወጥ መንገድ ሰዎችን በማዘዋወር በዝርፊያ ና አስገድዶ በመድፈር ክስ በተመሰረተበት ማህሙድ መሃመድ ተባለው የሶማሊያ ዜጋ በኢጣልያዋ የሲሲሊ ክፍለ ሃገር ዋና ከተማ ፓሌርሞ ፍርድ ቤት ተመሰከረበት ። ተከሳሹ በባህር ላይ ጉዞ ግፍ የፈፀመባቸው ኤርትራውያን በፓሌርሞው ፍርድ ቤት ቀርበው ባለፈው ሰኞ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል ። ለፍርድ ቤት ቃላቸውን የሰጡት 7 ኤርትራውያን ስደተኞች ናቸው ። ከመካከላቸው በተከሳሹ የተደፈረች የ18 ዓመት ልጃገረድ ትገኝበታለች ። ባለፈው ባለፈው ጥቅምት ወር በኢጣልያዋ ደሴት ላምፔዱዛ አቅራቢያ የተሳፈሩባት ጀልባ ሰጥማ ከሞቱት 366 ሰዎች መካከል በግለሰቡ የተደፈሩ ሴቶች ይገኙበታል ። ተክለ እዝጊ ገብረ እየሱስ ከሮም ዝርዝር ዘገባ አለው ።

ተክለ እዝጊ ገብረ እየሱስ

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሃመድ