1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርትራ መንግሥት ተቃዋሚዎች ሠልፍ በበርሊን

ረቡዕ፣ ግንቦት 12 2001

የኤርትራ ዴሞክራሲያዊ ሕብረትና የሲቢል ማሕበረሰብ ማሕበራት ያደራጁት ሠልፈኛ የጀርመን መንግሥት በፕሬዝዳት ኢሳያስ አፈወርቂ መንግሥት ላይ ተፅዕኖ እንዲያደርግም ጠይቀዋል

https://p.dw.com/p/HuIb

እዚሕ ጀርመን የሚኖሩ ኤርትራዉያን የሐገራቸዉን መንግሥት በመቃወም ዛሬ በርሊን ዉስጥ የአደባባይ ሠልፍ አድርገዋል።ከተለያዩ የጀርመን ከተሞች የተሰባሰቡት ሠልፈኞች እንደሚሉት የኤርትራ መንግሥት የሰብአዊ መብት ይረግጣል፥ የሐይማኖት መሪዎችን፥ ተቃዋሚ ፖለቲከኞችንና ጋዜጠኞች ያስራል።የኤርትራ ዴሞክራሲያዊ ሕብረትና የሲቢል ማሕበረሰብ ማሕበራት ያደራጁት ሠልፈኛ የጀርመን መንግሥት በፕሬዝዳት ኢሳያስ አፈወርቂ መንግሥት ላይ ተፅዕኖ እንዲያደርግም ጠይቀዋል።የበርሊኑ ወኪላችንን ይልማ ሐይለ ሚካኤልን እና የሰልፉን አደራጆች በስልክ አነጋግሪያቸዉ ነበር።

ነጋሽ መሐመድ/ይልማ ሐይለ ሚካኤል/ሂሩት መለሰ