1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤርትራ ስደተኞች በኢትዮጵያ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 16 2001

ስደተኞቹን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን ባለሥልጣናት፤ ዲፕሎማቶችና የርዳታ ድርጅት ተወካዮች ጎብኝተዋቸዉ ነበር።

https://p.dw.com/p/IXhq
አዋሳኙ ድንበርምስል AP

የኢትዮጵያና የኤርትራ ጦርነት ከተደረገ ወዲሕ በሺ የሚቆጠሩ ኤርትራዉያን ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ነዉ።ባለፈዉ ቅዳሜ የተከበረዉን የአለም ስደተኞች ቀን ምክንያት በማድረግ ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ ተጉዞ የነበረዉ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ እንደዘገበዉ ማይ-አይኒ በተባለዉ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ብቻ ከአስር-ሺሕ በላይ ኤርትራዉያን ስደተኞች ተጠልለዋል።ስደተኞቹን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን ባለሥልጣናት፤ ዲፕሎማቶችና የርዳታ ድርጅት ተወካዮች ጎብኝተዋቸዉ ነበር።

ጌታቸዉ ተድላ/ነጋሽ መሐመድ/ሂሩት መለሰ