1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚ

ኤርትራ እና ኤኮኖሚዋ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 12 2009

ዶክተር ሴት ካፕላን ሀገሪቱ ለግል ባለሀብቶች ቦታ እንደማትሰጥና መንግሥት በኤኮኖሚ ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ሊኖረው ይገባል የሚል መርህ እንደምታራምድ አስታውቀዋል ።

https://p.dw.com/p/2Ze76
Eritrea Bisha Mine bei Asmara
ምስል Reuters/T. Mukoya

Beri. Stockholm( Study on Eritrea Economy ) - MP3-Stereo

ኤርትራ የምትከተለው መርህ ወደ ሶሻሊዝም ያጋደለ ነው ሲሉ አንድ ምሁር አስታወቁ ። በኤርትራ ኤኮኖሚ ላይ ያተኮረ አንድ ጥናት በቅርቡ ያወጡት የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርስቲ መምህር፣ የዓለም ባንክ እና የአፍሪቃ ልማት ባንክ አማካሪ ዶክተር ሴት ካፕላን  ሀገሪቱ ለግል ባለሀብቶች ቦታ እንደማትሰጥና  መንግሥት በኤኮኖሚ ውስጥ ከፍተኛ ድርሻ ሊኖረው ይገባል የሚል መርህ እንደምታራምድ አስታውቀዋል ። ዓለም ዓቀፉ ማህበረሰብ የጣለባት እገዳ ባለሀብቶች በሀገሪቱ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዳያፈሱ እንቅፋት በመሆን በኤኮኖሚዋ ላይ ተጽእኖ ማሳደሩንም ለዶቼቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ ገልጸዋል ። ዶክተር ካፕላንን ያነጋገራቸው የስቶክሆልሙ ወኪላችን ቴድሮስ ምህረቱ ቀጣዩን ዘገባ አጠናቅሯል ።
ቴድሮስ ምህረቱ 
ኂሩት መለሰ