1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
12 ምስሎች
አዜብ ታደሰ | ሸዋዬ ለገሠ
ሐሙስ፣ ሰኔ 21 2010
https://p.dw.com/p/30Oai

የኢትዮጵያን እና የኤርትራን መቀራረብ የተለያዩ መንግሥታትና የፖለቲካ ተንታኞች በጎ ጅማሮ ታሪካዊ ሲሉ አወድሰዋል። ለሁለት አስርተ ዓመታት ተቋርጦ የነበረዉ የኤርትራና የኢትዮጵያ  ይፋዊና ዲፕሎማስያዊ ግንኙነት አንድ ርምጃ ከፍ ብሎ በመታየቱ መደሰታቸውን በጀርመን የጀርመን-አፍሪቃ ድርጅት ፕሬዚዳንት ዶክተር ኡሺ አይድ ገልጸዋል። እንዲያም ቢሆን ይህ አወንታዊ ክስተት ሊሆን የቻለዉ በአዲሱ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቀና እና ደፋር ርምጃ ብሎም የኤርትራዉ ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከኢትዮጵያ ወገን የቀረበላቸዉን የሰላም ጥያቄ በአዎንታ በመቀበላቸዉ ነዉ፤ ብለዋል።