1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኤድስ ስርጭት በዓለም ዙሪያና በኢትዮጵያ

ዓርብ፣ ኅዳር 20 2000

ከሰሀራ በታች በሚገኙ አንዳንድ የአፍሪቃ አገራት አሁን የኤድስ ስርጭት በተወሰነ ደረጃ እየቀነሰ ነው ። ሆኖም በአንዳንድ ሀገራት ለውጥ አልታየም ።

https://p.dw.com/p/E0mk
በኤድስ ወላጅ አልባ የሆነ ህፃን
በኤድስ ወላጅ አልባ የሆነ ህፃንምስል AP
UNAIDS እንዳስታወቀው በአሁኑ ሰዓት በዓለም ዙሪያ ኤድስን ከሚያስከትለው ኤች አይ ቪ ጋር የሚኖሩ ሰዎች ቁጥር ሰላሳ ሶስት ነጥብ ሁለት ሚሊዮን ደርሷል ። ድርጅቱ ዘንድሮ እንደገና አስተካክሎ ያወጣው ይህ አሀዝ ካለፈው ዓመቱ ጋር ሲነፃፀር በሰባት ሚሊዮን ገደማ ዝቅ ያለ ነው ።