1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእሁዱ የፈረንሳይ የመታሰቢያ ሰልፍ

ሰኞ፣ ጥር 4 2007

ፈረንሳይ ውስጥ በሽብር ጥቃት የተገደሉትን 17 ሰዎች ለማሰብ በሳምንቱ መጨረሻ በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ በፓሪስ አደባባይ ተገኝቶ ሃዘኑን፤ አንድ መሆኑን አሳይቶአል።

https://p.dw.com/p/1EJ7A
Paris Charlie Hebdo Terroranschlag Hommage Frankreich Trauer
ምስል picture-alliance/dpa


ሰልፉም በፈረንሳይ ታሪክ በርካቶች አደባባይ የወጡበት ሰልፍ እንደሆነ ነዉ የተነገረዉ። ህዝባዊ ሰልፉ ፤ ሽብርተኝነትን በማውገዝ፣ አንድነትን እና ነፃነትን በሰበከ ሁኔታ ፤ በሰላም ተካሂዶ ተጠናቋል። የዘር፣ የሐይማኖት ፣ የፖለቲካ ልዩነት ሳይገድባቸው፤ በአንድነት ሲቆሙ፤ በፈረንሳይ የሚኖሩ የውጭ ሀገር ዜጎችም ሰንደቅ አላማቸውን ይዘው በመውጣት አጋርነታቸውን አሳይተዋል። ይሁንና የባለፈውን ሳምንት ጥቃት ፈፃሚዎች፤ የአፍሪቃ ዝርያ ያላቸው ፈረንሳውያን መሆናቸው ከተነገር አንስቶ ፈረንሳይ ውስጥ የሚኖሩ በርካታ የሰሜን አፍሪቃ ፤ የእስልምና ሐይማኖት ተከታዮች ደህንነታቸው ስጋት ላይ እንደወደቀ ይናገራሉ። የፓሪሷ ዘጋቢያችን ዝርዝር ዘገባ ልካልናለች።


ሐይማኖት ጥሩነህ


ልደት አበበ
ተክሌ የኋላ