1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእሥራኤል ኢትዮጵያውያንን ያስቆጣው አድልዎ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 26 2001

ቤተ-እሥራኤላውያኑ በበኩላቸው ዛሬ ኢየሩሣሌም ውስጥ በአገሪቱ ፓርላማ ፊትለፊት በመሰለፍ ብሶታቸውን ገልጸዋል። ዝርዝሩን ዜናነህ መኮንን!

https://p.dw.com/p/JMdA
እየሩሳሌምምስል picture-alliance/ dpa

የእሥራኤል ኢትዮጵያውያን አይሁዶች "ቤተ-እሥራኤላውያን" በሰፈሩባት አገር በየጊዜው የሚገጥማቸው ዘረኛና የአድልዎ ድርጊት ብዙ ነው። ሆኖም አሁን ሶሥት የአይሁድ የሃይማኖት ትም/ቤቶች መቶ ገደማ የሚጠጉ ልጆቻችውን አንቀበልም ሲሉ የወሰዱት ዕርምጃ እነርሱን ብቻ ሣይሆን የእሥራኤልን መንግሥት ባለሥልጣናት ጭምር አስቆጥቷል። ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታኒያሁ ድርጊቱን ሞራል የጎደለው ሲሉ ነው የኮነኑት። ይህ ብቻ አይደለም መንግሥት ለት/ቤቶቹ የሚሰጠውን ድጎማ እንደሚቆርጥም ነው ያስጠነቀቀው። ቤተ-እሥራኤላውያኑ በበኩላቸው ዛሬ ኢየሩሣሌም ውስጥ በአገሪቱ ፓርላማ ፊትለፊት በመሰለፍ ብሶታቸውን ገልጸዋል። ዝርዝሩን ዜናነህ መኮንን!

Zenaneh Mokennen /MM

Negash Mohammed