1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእስረኞች መፈታትና የአዉሮጳ ኅብረት ምላሽ 

ዓርብ፣ የካቲት 2 2010

የአውሮጳ ህብረት የኢትዮጵያ መንግሥት እስረኞችን በይቅርታ ለመልቀቅ መወሰኑን አዎንታዊ እርምጃ ሲል አወደሰ። በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የፖለቲካ ተሀድሶንም እንደሚደግፍ አስታወቀ። ህብረቱ ከዚሁ ጎን ለጎን የተቃዋሚ ሰልፈኞች ጥያቄዎችም በውይይት እንዲፈታ አሳስበዋል። 

https://p.dw.com/p/2sQUS
Symbolbild EU
ምስል Getty Images/AFP/D. Roland

Ber.( Brussel) Release of Political Prisoners - MP3-Stereo

 

የአውሮጳ ህብረት የኢትዮጵያ መንግሥት እስረኞችን በይቅርታ ለመልቀቅ መወሰኑን አዎንታዊ እርምጃ ሲል አወደሰ። በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የፖለቲካ ተሀድሶንም እንደሚደግፍ አስታወቀ። የህብረቱ ቃል አቀባይ ካትሪን ሬይ ዛሬ ለዶቼቬለ በሰጡት አስተያየት ባለፉት ሳምንታት በሺህዎች የሚቆጠሩ እሥረኞች መፈታታቸው እንዲሁም ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ እና የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ አንዷለም አራጌን ጨምሮ ሌሎችንም ታራሚዎች ለመፍታት መወሰኑ ትክክለኛ አቅጣጫን የሚያሳይ እርምጃ ነው ብለዋል ከዚሁ ጎን ለጎን የተቃዋሚ ሰልፈኞችን ጥያቄዎችም በውይይት እንዲፈታ አሳስበዋል። 


ገበያዉ ንጉሴ
አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ