1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእስራኤል ውሳኔ ና አፍሪቃውያን ስደተኞችና

ሐሙስ፣ ጥር 15 2006

የእስራኤል ባለሥልጣናት አፍሪቃውያን ስደተኞች በሃገሪቱ በረሃማ ደቡባዊ ክፍል ወደ ሚገኘው የሆሎት የስደተኞች ማቆያ እንዲገቡ አዟል ። ባለሥልጣናት እንደሚሉት ወደ ዚህ መጠለያ ለገቡት ስደተኞቹ በቋሚነት የሚኖሩበት ቦታ እየተፈለገላቸው ነው ።

https://p.dw.com/p/1AwHi
ምስል Reuters

በፈቃደኝነት ወደ ሃገራቸው ለሚመለሱም የገንዘብ ማበረታታዎች ይሰጣቸዋል ። በአዲሱ የሆሎት መጠለያ እስከ ጥር ማብቂያ ድረስ በመቶዎች የሚቆጠሩ አፍሪቃውያን ስደተኞች ይገባሉ ተብሎ ይጠበቃል ። ስደተኞቹ በመጠለያው በሚቆዩበት ወቅት ተገን የጠየቁበት ማመልከቻ ይታያል ፤ የሚስጠጉዋቸው ሌሎች ሃገራትም ይፈለጉላቸዋል ። ስደተኞቹ ከመጠለያው መውጣትም ሆነ መግባት ቢፈቀድላቸውም በቀን የተወሰነ ጊዜ መፈረምና እዚያ ማደር ግዴታቸው ነው ። ስለ አጠቃላዩ ሁኔታ የሃይፋውን ዘጋቢያችንን ግርማ አሻግሬን በስልክ አነጋግረነዋል ።

ግርማው አሻግሬ

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ