1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእስራኤል ውጭ ጉዳዪ ሚኒስትር የአፍሪቃ ጉብኝት

ረቡዕ፣ ነሐሴ 27 2001

የእስራኤል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቪድጎር ሊበርማን በአምስት የአፍሪቃ አገራት የሚያደርጉትን ጉብኝት ዛሬ በኢትዮጵያ ጀምረዋል ።

https://p.dw.com/p/JNw1
አቪድጎር ሊበርማንምስል AP

ውጭ ጉዳዪ ሚኒስትር ሊበርማን በዚህ ጉብኝታቸው ከኢትዮጵያ በተጨማሪ ኬንያ ኡጋንዳ ናይጀሪያ እና ጋናም ይሄዳሉ ። ከርሳቸው ጋርም ሀያ የእስራኤል ነጋዴዎችና የኩባንያዎች ባለቤቶች አብረው ተጉዘዋል ። አንድ የእስራኤል ውጭ ጉዳዪ ሚኒስትር ከሀያ ዓመት ወዲህ ከሰሀራ በታች በሚገኙ የአፍሪቃ ሀገራት ጉብኝት ሲያደርግ ሊበርማን የመጀመሪያው ናቸው ። የሊበርማን የኢትዮጵያ እና የሌሎች አራት የአፍሪቃ አገራት ጉብኝት ዓላማ ላይ በማተኮር የእየሩሳሌሙ ወኪላችን ዜናነህ መኮንን ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል ።

ዜናነህ መኮንን ፣ሂሩት መለሰ