1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእስራኤል ጦር ከጋዛ መውጣቱና የአረብ ሊግ

ሰኞ፣ ጥር 11 2001

እስራኤል በሐማስ ላይ ከፍትኩት ባለችው መጠነ ሰፊ የ22 ቀናት ወታደራዊ ዘመቻ የሟቾች ፍልስጤማውያን ቁጥር ከአንድ ሺህ ሶስት መቶ መብለጡ ሲነገር፤ አምስት ሺህ ቁስለኞችም መቆጠራቸው ተዘግቧል። በትንሹ 22 ሺህ የሚጠጉ የግልና የመንግስት ህንፃዎቿ የተጎዱ አለያም የተደረመሱ መሆናቸውን DPA የፍልስጥኤም ማዕከላዊ የመረጃ ቢሮን ጠቅሶ ዘግቧል።

https://p.dw.com/p/Gbag
የእስራኤል ወታደር ጓዙን ሸክፎ
የእስራኤል ወታደር ጓዙን ሸክፎምስል AP
የእስራኤል ጦር ትናንትና ማታና ዛሬ ማለዳ ከጋዛ መውጣት መጀመሩ ተገለፀ። ጋዛ በሶስት ሳምንቱ የቦንብ ጥቃት በትንሹ ሃያ ሁለት ሺህ የሚጠጉ የግልና የመንግስት ህንፃዎቿ የተጎዱ አለያም የተደረመሱ መሆናቸውን DPA የፍልስጥኤም ማዕከላዊ የመረጃ ቢሮን ጠቅሶ ዘግቧል። ዛሬ ኩዌት ውስጥ በተጀመረው የአረብ ሊግ ጉባኤ ላይ ደግሞ፤ የኩዌቱ አሚር ሼክ ሳባህ “እስራኤል የጦር ወንጀለኛ ናት” ሲሉ፣ የሶሪያው ፕሬዚዳንት ባሽር አል አሳድ “እስራኤል በአሸባሪ መዝገብ ውስጥ መስፈር አለባት” ሲሉ ተናግረዋል። ጉባኤው እስራኤልን በተመለከተ ልዩነት እንደነበረበትም ተጠቅሷል።