1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

 የእስቴ መስጅዶች ቃጠሎና መፍትሔዉ 

ረቡዕ፣ ጥር 29 2011

ደቡብ ጎንደር እስቴ ወረዳ መካነ እየሱስ ከተማ በሚኖሩ ሙስሊሞች ላይ ባለፈዉ ዕሁድ የተፈፀመው ወንጀል ማንንም እንደማይወክል የዞኑ የኮሙዩኒኬሽን ፅፈት ቤት አስታወቀ፡፡በአንድ የሙስሊም ሠርግ ላይ ክርስትናን የሚነቅፍ ድርጊት ተፈፅሟል በሚል ሰበብ ከተማይቱ ዉስጥ የሚገኙ ሁለት መስጂዶች ተቃጥለዋል።

https://p.dw.com/p/3Cm2A
Fasil Schloss Gonder Äthiopien
ምስል DW/Azeb Tadesse Hahn

ደቡብ ጎንደር እስቴ ወረዳ መካነ እየሱስ ከተማ በሚኖሩ ሙስሊሞች ላይ ባለፈዉ ዕሁድ የተፈፀመው ወንጀል ማንንም እንደማይወክል የዞኑ የኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ በአንድ የሙስሊም ሠርግ ላይ ክርስትናን የሚነቅፍ ድርጊት ተፈፅሟል በሚል ሰበብ ከተማይቱ ዉስጥ የሚገኙ ሁለት መስጂዶች ተቃጥለዋል።የሙስሊሞች ናቸዉ የተባሉ ሱቆች ተዘርፈዋልም። አንድ የከተማዋ ነዋሪ ዛሬ ለ «DW» በስልክ እንደነገሩት ከተማዋ ተረጋግታለች። የደቡብ ጎንደር ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን  ኃላፊ አቶ ጥላሁን ደጀኔ በበኩላቸው ጠቡን ለማብረድ ትናንትና ባለሥልጣናት በተገኙበት ውይይት ተደርጓል። በዉይይቱ ወቅት የተቃጠሉ መስጂዶችን  ህብረተሰቡ በጋራ ለመገንባት ቃል ገብቷልም። የባሕር ዳሩ ወኪላችን  ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።

ዓለምነዉ መኮንን 

ነጋሽ መሐመድ 

ኂሩት መለሰ