1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእነ በቀለ ገርባ የፍርድ ቤት ውሎ

ረቡዕ፣ ኅዳር 7 2009

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ የቀድሞ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ በእነ ጉርሜሳ አያኖ መዝገብ የተከሰሱ 22 ተከሳሾች ላይ የአቃቤ-ሕግ ምስክሮች ማሰማት ጀመረ።

https://p.dw.com/p/2Sn1z
Äthiopien Journalisten Martin Schibbye und Johan Persson
ምስል AP

(Beri, Addis Ababa)Ethiopian Court starts hearing witness on Bekele Gerba et al - MP3-Stereo

አቃቤ-ሕግ ምስክር የማሰማት ሒደቱ በዝግ ችሎት ይሁንልኝ ቢልም ፍርድ ቤት ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል።  የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ችሎት የአቃቤ-ሕግን የመጀመሪያ ምስክር በግልፅ ችሎት ዛሬ ጠዋት ሰምቷል። ችሎቱ የምስክሮችን ቃል እስከ ኅዳር 13 ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት ይሰማል። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የፍርድ ቤቱን ዉሎ ተከታትሎት ነበር።
ዮሐንስ ገብረ እግዚዓብሔር 
እሸቴ በቀለ
ነጋሽ መሐመድ