1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእነ አቶ ጀዋር የፍርድ ቤት ዉሎ

ማክሰኞ፣ ጥር 4 2013

ድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ ባለፈዉ ሰኔ 22 በተገደለ ማግስት በኦሮሚያ ክልል ሁከት ቀስቅሳችኋል የሚል ክስ ከተመሰረተባቸዉ ተጠርጣሪዎች መሐል አቶ ጀዋር መሐመድና አቶ በቀለ ገርባ «ለደሕንነታችን እንሰጋለን» በሚል ባለፉት 4 ተከታታይ ቀጠሮዎች ፍርድ ቤት አልቀረቡም ነበር።

https://p.dw.com/p/3npUB
Äthiopien Oberlandesgericht Lideta
ምስል Seyoum Getu/DW

ከተከሳሾቹ ሁለቱ 4ቴ፣ ሁለቱ 2ቴ ፍርድ ቤት አልቀረቡም ነበር

 በታዋቂዉ የኦሮሞ ፖለቲካ አቀንቃኝና በኦሮሞ ሚዲያ ኔትዎርክ መስራች ጀዋር መሐመድ መዝገብ የተከሰሱት ፖለቲከኞችና ደጋፊዎቻቸዉ ዛሬ ፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ቀረቡ።ድምፃዊ ሐጫሉ ሁንዴሳ ባለፈዉ ሰኔ 22 በተገደለ ማግስት በኦሮሚያ ክልል ሁከት ቀስቅሳችኋል የሚል ክስ ከተመሰረተባቸዉ ተጠርጣሪዎች መሐል አቶ ጀዋር መሐመድና አቶ በቀለ ገርባ «ለደሕንነታችን እንሰጋለን» በሚል ባለፉት 4 ተከታታይ ቀጠሮዎች ፍርድ ቤት አልቀረቡም ነበር።አቶ ሐምዛ አዳነ እና አቶ ሸምሰዲን ጣሐ ደግሞ በሁለት ቀጠሮዎች ፍርድ ቤት አልቀረቡም።ተከሳሾቹ በኃይልም ቢሆን ተገድደዉ እንዲቀርቡ ፍርድ ቤቱ በማዘዙ ከፍተኛ ቁጥጥር በተደረገበት በዛሬዉ ችሎት ተከሳሾቹ በሙሉ ቀርበዋል።

ስዩም ጌቱ 

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ