1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የእንሰሳት ሕክምናና ምርምር

ረቡዕ፣ ነሐሴ 25 2008

በመቀሌ ዩንቨርስቲ የእንስሳ ሕክምና ኮሌጅ ከብቶች የተፈለገዉን ዓይነት ጾታና በተፈለገዉ ጊዜ እንዲወልዱ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ላይ እየሰራ መሆኑ ተመለከተ።

https://p.dw.com/p/1Jt0e
Äthiopien Mekelle University in Mek'ele - Tiermiedizin
ምስል DW/Y. Geberegziabeher

የእንሰሳት ህክምናና ምርምር


ትምህርት ክፍሉ በዘመናዊ ቤተ- ሙከራዎች የተደራጀ ሲሆን በርካታ ችግር ፈቺ ምርምሮችን በማካሄድ ላይ እንደሆነም ተገልፆአል። ከምርምሮቹ አንዱ ደግሞ ከብቶች መኖ በሚገኝበት ወራት ብቻ እንዲወልዱ የሚያደርግ ምርምር እንደሆነ ነዉ የተመለከተዉ። «ሲንክሮናዜሽን» በሚል መጠርያ የሚታወቀዉ ይህ ምርምር ከብቶች የሚወልዱበትን ጊዜ ወስኖ ላምዋን «ሆርሞን » በመቆጣጠር በተፈለገዉ ወራት አርግዛ በተፈለገዉ ወራት እንድትወልድ የሚያደርግ መሆኑ ነዉ የተነገረዉ። መቀሌ የእንስሳ ሕክምና ኮሌጅ የተገኘዉ የአዲስ አበባዉ ወኪላችን የኮሌጁን ዲንና ተመራማሪ ዶ/ር በሪሁ ገብረኪዳንን አነጋግሮ ሰፋ ያለ መሰናዶ ልኮልናል።


ዮኃንስ ገ/እግዚአብሄር


አዜብ ታደሰ