1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአራት ዩኒቨርስቲዎች የጋራ ፕሮጀክት

ማክሰኞ፣ ጳጉሜን 5 2011

በ2012 በወለጋ፣ ምዕራብ ሸዋ በኢሉ አባቦር እና ዩኒቨርሲቲዩቹ በሚገኙባቸው ሌሎች ዞኖች 28 በሚሆኑ ወረዳዎች የግብርና ልማት ጣቢያዎችን በማቋቋም ስራው እንደሚጀምር አመልክቷል፡፡ 4ቱም ዩኒቨርሲቲዎች ከኦሮሚያ መስተዳድር እና የተክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሚንስቴር ጋር  በትብብር ይሰራሉ። በመጪው ዓመትም 21ሺ እስንሳትን ለማዳቀል መታቀዱም ተነግሯል።

https://p.dw.com/p/3PLEM
Uganda Flüchtlingslager in Nakivale
ምስል DW/S. Schlindwein

የአራት ዩኒቨርስቲዎች የጋራ ፕሮጀክት

 

በኦሮምያ መስተዳድር ውስጥ የሚገኙ አራት የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በምዕራብ ኦሮሚያ የእንስሳት ምርትን ለማሳደግ ያግዛል የተባለ ለአስር ዓመታት የሚቆይ የልማት ፕሮጀክት በጋራ ለማከናወን በመቱ ዪኒቨርሲቲ ውል ተፈራረሙ፡፡ በጋራ ለመሥራት ከተስማሙት ውስጥ፣ የአምቦ ፣የጅማ እና የወለጋ ዩኒቨርስቲዎች ይገኑበታል፡፡ፕሮጀክቱ የእንስሳት ዝርያዎችን ለአርሶ አደሩ በማቅረብ የወተትና ስጋ ምርታማነትን የማሳደግ ዓላማ እንዳለው በመቱ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ረዳት ፕሮፈሰር ጸጋዬ ባርከሳ  ለዶቼቬለ ተናግረዋል። የወለጋ፣አምቦ፣መቱና የጅማ ዩኒቨርሲቲዎች በምዕራብ ኦሮሚያ ያለውን የእንስሳት ምርት ለማሳደግ ያስችላል ያሉትን የጋራ ፕሮጀክት ለቀጣይ አስር ዓመታት አብሮ ለመስራት አቅዷል፡፡ በመቱ ዩኒቨርሲቲ አስተባባሪነት የተጀመረው ይህ የልማት ፕሮክጅት ለአካባቢው አርሶ አደሮች የተሻለ ምርት ሊያስገኙ የሚችሉ የእንስሳት ዝርያዎችን የማቅረብ ዓላማ እንዳለው የፕሮጀክቱ ሓላፊና በመቱ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና የማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዚዳንት ረ/ፕ ጸጋዬ ባርከሳ በስልክ ተናግረዋል፡፡  የእንስሳት ዝርያዎችን ከማቅረብ በተጨማሪም ዘመናዊ የስጋና ወተት ምርት ማቀነባበርያን በማቋቋም ለአካባቢው ማህበረሰብና ሌሎች ክልሎች ምርቱን ማቅረብ ደግሞ ሌላው የፕሮጀክቱ ዓላማ እንደሆነም ገልጸዋል።

በ2012 ዓ፣ም  በወለጋ፣ ምዕራብ ሸዋ፣ በኢሉ አባቦር እና ዩኒቨርሲቲዩቹ በሚገኙባቸው ሌሎች ዞኖች 28 በሚሆኑ ወረዳዎች የግብርና ልማት ጣቢያዎችን በማቋቋም ስራው እንደሚጀምር አመልክቷል፡፡ አራቱም ዩኒቨርሲቲዎች ከኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እና የተክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሚንስቴር ጋር  በትብብር የሚሰሩ ሲሆን በመጪው ዓመት ማህበራሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ 21ሺ እስንሳትን ለማዳቀል መታቀዱንም ረዳት ፕሮፈሰሩ አስታውቀዋል፡፡የአካባቢውን ወጣቶች በማደረጃትም የእንስሳት መኖ በማቅረብ ስራ እንዲሰማሩ ይደረጋል ብለዋል፡፡

በምስራቅ ወለጋና በጊምቢ ስራውን ተግባራዊ በማድረግ የዞኑን አርሶ አደር የእንስሳት የምርት መጠን ለማሳደግ እንደሚሰሩ የተናገሩት ደግሞ የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ፕረዚዳንት ዶ.ር ሐሰን የሱፍ ናቸው፡፡ የወለጋ ዩኒቨርሲቲ ከምስራቅና ምዕራብ ወለጋ ዞን የግብርና ጽ/ቤቶች ጋር ምርምሮችን በመስራት ያለውን የእንስሳት ምርት በቴክኖሎጅ በማስደገፍ በምዕራቡ የሀገሪቱ ክፍል ምርቱን በማቅረብ ዩኒቨርሲቲው የበኩሉን ድርሻ ይወጣልም ብለዋል፡፡

የእንስሳት ምርት ለማሳደግ የተሰማራው ፕሮጀክቱ አንድ ቢሊየን ብር በጀት የሚስፈልገው ሲሆን ወጪው በኦሮሚያ ክልል፣በተክኖሎጂና ኢኖቬሽን ሚንስቴር እና በአራቱም ዩኒቨርሲቲዎች የሚሸፈን ይሆናል ተብሏል፡፡

 

ነጋሳ ደሳለኝ

ኂሩት መለሰ

እሸቴ በቀለ