1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦህዴድ መግለጫና አንድምታዉ

ረቡዕ፣ ጥር 30 2010

የኦሮሞ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት ኦህዴድ ከ10 ቀናት የማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በኋላ በትናንትናዉ እለት ያወጣዉ መግለጫ ብዙወችን እያነጋገረ ነዉ። መግለጫዉን አንዳንዶች« ተስፋ ሰጪ» ሲሉት አንዳንዶች ደግሞ በተፈፃሚነቱ ላይ ጥያቄ ያነሳሉ።

https://p.dw.com/p/2sHhZ
Äthiopien Irreecha Feierlichkeiten
ምስል DW/Y. Gebregzihabher

Is OPDO in Reform? - MP3-Stereo



የኦሮሞ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት «ኦህዴድ» ላለፉት አስር  ቀናት በአዳማ ከተማ በማዕከላዊ ኮሚቴ ደረጃ ሲያካሂድ የቆየዉን ስብስባ በትናንትናዉ ዕለት ማጠናቀቁን ገልጿል። ስብሰባዉ ቢጠናቀቅም ድርጅቱ በስብሰባዉ ማጠናቀቂያ ላይ ያወጣዉ መግለጫ ግን ማነጋገሩን ቀጥሏል። የኦሮሞ  ሙህራን፣ የፀጥታ አካላት፣ የመንግስት ሰራተኖች፣ ወጣቶች፣ የፖለቲካ ፓርቲወች በአጠቃላይ በዉጭም ይሁን በሐገር ዉስጥ የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆችንና የተለያዩ  የህብረተሰብ ክፍሎችን የፖለቲካ ልዩነት ሳይገድባቸዉ በክልሉ አስተዋፅኦ ማበርከት እንዲችሉ በር መክፈቱን ኦህዴድ በመግለጫዉ አትቷል ። ድርጅቱ «ለክልሉ ብሎም ለሀገሪቱ ሰላም ልማትና ዴሞክራሲ ጉዞ ስኬት እንዲሁም ለህዝቦች እኩል ተጠቃሚነት ከምንጊዜዉም በላይ ልሰራ ተዘጋጅቻለሁ» ሲልም  አመልክቷል። ይህ የኦህዴድ ድርጅታዊ መግለጫ ላላፉት 3 ዓመታት በተቃዉሞ ለቆየዉ የኦሮሚያ ክልልም ይሁን ለሀገሪቱ «ተስፋ ሰጭ ይመስላል» ሲሉ የኦሮሚያ ስቴት ዩንቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንትና የፖለቲካ ምሁር ዶክተር ሚልኬሳ ሚዳና ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል። «ኦህዴድ የኢህአዴግ አባል ነዉ።አንድ የኢህአዲግ አባል ከሆነ ድርጅት፤ሙህራንን ጠቅሶ የአካሄዳችሁት የከፈላችሁት መሰዋዕትነት አልወደቀም አሁንም ያነገር የታገላችሁለት ዝም ብሎ አልቀረም ፍሬ አፍርቷል።አሁንም ያንን ቀጥሉ ፣አብረን እንስራ፣ወጣቱንም የህብረተሰብ ክፍል እየጠቀሱ በፍትህ አካላትም «ሪፎርም» ማካሄድ እስከ ቀበሌ ድረስ ፤ይህ ሁሉ የአቃቬ ህግ ፣የፍትህ ስርዓቱ ብዙ ነገር እንደገና መከለስ አለበት ።ይህ ነገር በይዘቱም ለየት ይላል አካሄዱም ለየት ይላል፣«አድሬስ »ያደረጉትም እና በአጠቃላይ እኔ የዴሞክራሲ ተስፋ በኢትዮጵያ ላይ የተጫረ ይመስለኛል።»
ኦህዴድ በአጠቃላይ በፍትህ ስርዓቱ ፣ በሙስና፣ በእኩል ተጠቃሚነትና በአሳታፊነት ዙሪያ በመግለጫዉ ያነሳቸዉ ጉዳዮች፤ በክልሉ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታዩ ያሉ መጠነኛ ለዉጦችን አጠናክሮ ለመቀጠል ያስችላል ብለዋል። በአስተሳሰብና በፖለቲካ ልዩነት የተነሳ  «እኛ እና እነሱ » የሚለዉን በጥርጣሬና በጠላትነት መተያየት በማስቀረት ሁሉም የድርሻዉን እንዲያበረክት በር ይከፍታል ሲሉ አስረድተዋል። «አሸናፊና ተሸናፊ ተደርገዉ ነበር የሚወሰዱት። ከዚህ በፊት በኢትዮያ ታሪክ  ያሸነፈ ስልጣን መያዝ ነዉ፤ ከዚያ ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ነዉ።ሌላዉን የጎሪጥ እንደ ጠላት ማየት ነዉ።ከዚያ አሸባሪ እከሌ እየተባለ ስንት ነገር አይተን ነበር።አሁን ያ ሁሉ ጠባብ ፣ትምክህተኛ ቀርቶ አሁን ደግሞ ጥሪ ነዉ የተደረገላቸዉ።ለተቃዋሚ ፓርቲወች ፣ዉጭ ለሚኖሩ በሀገር ዉስጥ ለሚኖሩ አብረን እንስራ በሀገራችን በኦሮሞ ህዝብ ጉዳይ አብረን እንስራ የእንነጋገር ጥሪ ነዉ የተደረገ።ይህ በጣም ትልቅ ዉጤት ነዉ።በእርግጥም ተስፋ የሚሰጥ ዉሳኔ ነዉ። ከዚህ በኋላ ከማን ምን ይጠበቃል ማነዉ« ፋሲሊቴት» የሚያደርገዉ የሚለዉ ነገር ነዉ የሚቀረዉ።»
ኦህዴድ ከመግለጫዉ ባሻገር  ለቀድሞዉ ፕሬዝዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ የወሰነዉ የጥቅማጥቅም ዉሳኔም ድርጅቱ ራሱን ወደ ለዉጥ እያመጣ መሆኑን አንዱ ማሳያ ነዉ ብለዋል። 
ስማቸዉ እንዲጠቀስ ያልፈለጉና በወጣትነት እድሜ ክልል የሚገኙ የክልሉ ነዋሪ ግን የመግለጫዉ ይዘት ጥሩ ቢሆንም ተፈፃሚነቱ ላይ ግን ጥርጣሬ ኣላቸዉ። ለዚህም ከአሁን ቀደም ቃል የተገባዉንና ተፈፃሚ ያልሆነዉን  የኦሮሚያ ወጣቶች «ፈንድ» ለአብነት ያነሳሉ።

Äthiopien Irreecha Feierlichkeiten
ምስል DW/Y. Gebregzihabher

«ኦህዴድ ለየት ብሎ የቀረበበት ነዉ።በመግለጫነቱ  ስናየዉ ማለት ነዉ።ህብረተሰቡ የሚፈልገዉ ነገር ምንድነዉ ፤ሁሌ የተስፋ ቃል መደርደር ብቻ በቂ አይሆንም።የወጣቱንም የህብረተሰቡንም ጥያቄ የሚመልስ አይመስለኝም። አሁንም ህዝቡ የሚፈልገዉ ምንድነዉ ፤መግለጫ በማንበብ ሳይሆን የተግባር ስራ ነዉ።የሚፈልገዉ መሬት ላይ እዉነታ ነዉ የሚፈልገዉ።» ካሉ በኋላ ነዋሪዉ አያይዘዉም
«የኢትዮጵያ ፓርላማ ለወጣቶች ብሎ «ፈንድ» አስር ቢሊዮን ብር መድቦ ነበር።አንድም ወጣት በዚህ ተጠቃሚ አልሆነም ።ሁሌ ተስፋ ነዉ።አስር ቢሊዮን ብር ቀላል ነገር አይደለም ብዚ ወጣት ስራ ሊያስይዝ ይችል ነበር።ተስፋ ሁሌም አለ።ወሬ ብቻ እንዳይሆን ነዉ።ወደፊት ከተሰራበት ጥሩ ነዉ» ብለዋል
እንደ ዶክተር ሚልኬሳ ተፈጻሚነቱን በተመለከተ የግንባሩን ሌሎች አባል ድርጅቶች ስምምነትና እገዛ የሚጠይቅ በመሆኑ ተግዳሮት አለዉ። ያም ቢሆን ግን ይህ ርምጃ በህዝቡ ትግል የተገኜ  በመሆኑ ለተግባራዊነቱም«ህዝቡ ጠንክሮ ሊታገል ይገባል»ነዉ ያሉት።


ፀሐይ ጫኔ
አዜብ ታደሰ