1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን በወቅታዊ ጉዳይ መምከርዋ

ሐሙስ፣ የካቲት 5 2012

በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ውይይት ተካሄደ። የውይይት መድረኩ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የስብከተ ወንጌል እና ሃዋርያ ተልዕኮ መምሪያ አስተባባሪነት የተዘጋጀ መሆኑም ታዉቋል።

https://p.dw.com/p/3Xjiw
Äthiopien Addis Abeba | Abune Mathias, Patriarch der Orthodoxen Kirche
ምስል DW/G. Tedla

ችግሮችን ማረም፣ መፍታትና ማስተካከል አስፈላጊ ነዉ

በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ትኩረቱን ያደረገ ውይይት ተካሄደ። የውይይት መድረኩ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የስብከተ ወንጌል እና ሃዋርያ ተልዕኮ መምሪያ አስተባባሪነት የተዘጋጀ መሆኑም ታዉቋል። በዉይይቱ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባቶች፣ ሊቃውንት እና ምሁራን ተሳትፈዋል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጽዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ፥ በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች እየተከሰቱ ያሉ ችግሮችን ማረም፣ መፍታትና ማስተካከል አስፈላጊ መሆኑን አብክረዉ ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጽ/ ቤት ኃላፊ ብፁዕ አቡነ ያሬድ በበኩላቸው፥ በአሁኑ ወቅት የሚስተዋሉ መሰል ችግሮችን በጥናት በመታገዝ መፍታት እንደሚገባ ጠቁመዋል። 

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለጊዮርጊስ

አዜብ ታደሰ

ሸዋዩ ለገሠ