1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

Merga Yonas Bula
ረቡዕ፣ ጥር 3 2009

የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት አንቀፅ 49/5/ ኦሮሚያ ክልል አዲስ አበባ ላይ ያላትን ልዩ ጥቅሞችን ይጠቅሳል። ልዩ ጥቅም ማኅበራዊ አገልግሎቶችን ጨምሮ የተፈጥሮ ሐብቶችን እንደሚያጠቃልል ረቂቁ ያስቀምጣል።

https://p.dw.com/p/2Vdxm
Äthiopien Ministerpräsident Hailemariam Desalegn
ምስል Getty Images

M MT/ Oromia Special Interest on Addis Ababa - MP3-Stereo

ይሁን እንጅ ይህን ሊዩ ጥቅም የሚዘረዝር የህግ ማዕቀፍ እስካሁን አለመዉጣቱ ለብዙ ግጭቶች መንስዔ መሆኑን የህግና የፖለቲካ ተንታኞች ያመለክታሉ። በክልሉ ከጥቂት ጊዜ በፊት ተቀስቅሶ ለነበረዉ የፖለቲካ አለመረጋጋትም አንዱ ምክንያት መሆኑንም ተንታኞቹ አክለው ይጠቁማሉ።

ይህንንም ችግር ለመፍታት የአገሪቱ ፕሬዝደንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ልዩ ጥቅሙን በተመለከተ በዚህ ዓመት ሕግ እንደሚወጣ ጠቅሰዉ ነበር። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝም ከጥቂት ቀናት በፊት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ልዩ ጥቅሙን የሚወስነው ሕግ የመጀመሪያው ረቂቅ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።

አሁን የተዘጋጀዉ ረቅቅ ህግ ሊዩ ጥቅሙን ያስከብር ይሆን ብለን በኦሮሚያ ክልል በተለያየ አካባቢ ያሉትን ወጣቶች አነጋግረን ነበር። «ቤት ሲገነባም ቢሆን እርሻ መሬት ሲታረስ የምወስነዉ እኔ ነኝ» የሚሉት የናጆ ነዋሪ በልዩ ጥቅሙ ላይ መደረግ አለበት ያሉትን ሲያብራሩ፣ «ስሌ ፍንፍኔ  የሚወስኑት የካቢኔ አባላት ሳይሆኑ መወሰን ያለበት የኦሮሞ ህዝብ ብቻ ነዉ። ይህ ሁሉ ደም ፈሶበት የካብኔ አባላት በሚፈልጉት መንገድ ተወያይተው ቢወስኑም ህዝብ ለነሱ ውሳኔ ጆሮ አይሰጥም።»

አሁን የተዘጋጀዉ ረቅቅ ህግ ለተከሰተዉ ችግር መፍትሔ ይሆን ይሆናል ብዬ አልጠብቅም የሚሉት ደግሞ ሌላ የአዳማ ነዋሪ ናቸዉ።
የኢትዮጵያ መንግስት ረቂቁን ህግ ለማዉጣት «የህግና የስነመግባር ስልጣን ይጎድለዋል የሚሉት የሕግ ባለሙያ ዶክተር ፀጋዬ ራጋሳ አራርሳ ናቸዉ። ዴሞክራሲያዊ  ስርዓት ቢኖርም እንኳን ልዩ ጥቅሙ ህግ በማዉጣት ብቻ  የሚመመለስ ሳይሆን፣  መስተካከል ያለበት ታሪካዊ የሚሉት ስህተት ሊታረሙ እንደሚገባ ዶክተር ፀጋዬ ጠቁመዋል። ተዘጋጅተዋል የተባለዉ ረቅቅ ላይ የበለጠ መረጃ እንድሰጡን የክልሉም ሆነ የፌዴራል ያሉት የመረጃ ባለስጣናትን ለማነጋገር ያደርገነዉ ሙከራ ለግዜዉ አልተሳካም።

መርጋ ዮናስ 

አርያም ተክሌ