1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦሮሚያ ም/ቤት አባላት ያለመከሰስ መብት መነሳት

Merga Yonas Bulaዓርብ፣ ሰኔ 3 2008

ጨፌ ኦሮሚያ ትላንትና ባካሄደዉ የ1ኛ ዓመት 5ኛ የሥራ ዘመን፣ 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባ የሁለት ከፍተኛ አመራሮች ያለመከሰሰ መብት አንስቷል።

https://p.dw.com/p/1J4Xa
Wahl in Oromia Äthiopien 23.Mai 2010
ምስል DW

[No title]

ያለመከሰስ መብታቸው የተነሳውም በምክትል ፕሬዚደንት ማዕረግ የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ የነበሩት አቶ ዘላለም ጀማነ እና የሱሉልታ ከተማ ምክትል ከንቲባ የነበሩት አቶ ዲሮ ደሜ ናቸዉ። አቶ ዲሮ ደሜ የሱሉልታ ከተማ ከንቲባ እና በምዕራብ ሸዋ ዞን ጀልዱ ወረዳ የጨፌ ተወካይ በነበሩት ወቅት ስልጣናቸውን <<ያለአግባብ በመጠቀም ስለተጠረጠሩ በፀረ-ሙስና ኮሚሽኑ ጥያቄ መሰረት የኦሮምያ ምክር ቤት ያለ መከሰስ መብታቸውን ማንሳቱን የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።


አቶ ዘላለም ጀማነም ሥልጣናቸውን አለአግባብ በመጠቀም ኃብት አካብተዋል ተብሏል። ተጠርጣሪው አቶ ዘላለም ጀማነ ዛሬ በብሾፍቱ ከተማ በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ ተዘግቧል ። የመከሰስ መብቱ ሲነሳ አካሄዱ እንዴት እንደነበር በጫፌ ኦሮምያ የኮሙኒኬሸን እና እንፎርሜሸን ባለሙያ አቶ ሃብታሙ ደምሴ ለዶቼ ቬሌ አብራርተዋል፣ «አካሄዱ ችግር አልነበረዉም። በዚህ ጉዳይ ላይ ጥያቄ የማቅረብ መብት ያላቸው እንደ መንግስት ተቋም ሁለት አካል ናቸው። አንዱ የፍትህት ቢሮ ስሆን ሌላዉ ደግሞ በህግም ተደንግጎ መብቱ ያለዉ የኦሮምያ የስነ ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ነዉ። ለጨፌ ጥያቄ ሲያቀርቡ፣ በምርመራም የተደረሰባቸዉ ጉዳዮችም ቀርበው፣ ተጨባጭ ማስረጃዎችም ከቀረቡ በኋላ የጨፌ አባላት ከተወያዩበት በኋላ ነዉ ያለመከሰስ መብታቸው መነሳት የቻለዉ።»


የጨፌ ኦሮሚያ ያለመከሰስ መብት የማነሳት ርምጃ ከተባለዉ የሙስና ክስ ይልቅ የፖለቲካ እንድምታ አለዉ የሚሉት ጉዳዩን በቅርበት የሚከታታሉት የፖለትካ ተንታኝ አቶ ገረሱ ቱፋ ናቸዉ። የነዚህ ግለሰቦች ያለመከሰስ መብት መነሳት ተደምሮ የክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንት መነሳታቸዉ ለፓርቲዉም ሆነ ለማህበረሰቡ ብዙ እንድምታ እንዳለዉ ይናገራሉ። ዝርዝሩን ከድምጽ ዘገባዉ ያዳምጡ።

Oromo Proteste in Äthiopien
ምስል Oromia Media Network

መርጋ ዮናስ

ሒሩት መለሰ