1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦሮሞ ማሕበረሰብ ተቃውሞ በለንደን

ሐሙስ፣ ኅዳር 30 2008

በኢትዮጵያ ኦሮሚያ ክልል በመንግስት የተዘጋጀውን ማስተር ፕላን እና የመልካም አስተዳደር ጉድለቶች ምክንያት በማድረግ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ አሁንም ቀጥሏል። ተቃውሞው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን ጨምሮ በተለያዩ የክልሉ ከተሞች ተስፋፍቷል።

https://p.dw.com/p/1HLYN
Berlin Demonstration von Oromo-Aktivisten
ምስል DW/H. Kiesel

[No title]

ከገለልተኛ ወገን ማጣራት ባይቻልም የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ የሟቾች ቁጥር ከለት ወደ ዕለት እየጨመረ መሆኑን በማህበራዊ ድረ-ገጾች የተሰራጩ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን መንግስት የወሰደውን እርምጃ በመቃወም ድምጻቸውን በማሰማት ላይ ናቸው። በብሪታኒያ ዋና ከተማ ለንደን ዛሬ ተመሳሳይ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል። በለንደን ዛሬ የተካሄደውን የተቃውሞ ሰልፍ የዶይቼ ቬለ ወኪል ድልነሳው ጌታነህ ተመልክቶታል።

ድልነሳው ጌታነህ

እሸቴ በቀለ

ሒሩት መለሰ