1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ ሊቀመንበር ዳግም ቤት ይቆዩ?

ቅዳሜ፣ ሐምሌ 25 2012

ከቀናት ቆይታ በኋላ ወደ ጽህፈት ቤታቸው ተመልሰው የነበሩት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በድጋሚ በጸጥታ ኃይሎች ወደ ቤታቸው መወሰዳቸውን ግንባሩ አስታወቀ። አቶ ዳውድ በጸጥታ ኃይሎች ተገደው ወደ ቤት እንዲመለሱ የተደረጉት «ለደህንነታቸው ሲባል ነው» የግንባሩ ቃል አቃባይ ቀጄላ መርዳሳ ።

https://p.dw.com/p/3gH2G
Äthiopien Treffen Volksgruppe der Oromo Dawud Ibssa
ምስል DW/S. Muchie

ከቀናት ቆይታ በኋላ ወደ ጽህፈት ቤታቸው ተመልሰው የነበሩት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ በድጋሚ በጸጥታ ኃይሎች ወደ ቤታቸው መወሰዳቸውን ግንባሩ አስታወቀ። አቶ ዳውድ በጸጥታ ኃይሎች ተገደው ወደ ቤት እንዲመለሱ የተደረጉት «ለደህንነታቸው ሲባል ነው» የሚል ምላሽ ማግኘታቸውን የግንባሩ ቃል አቃባይ ቀጄላ መርዳሳ ለዶይቸ ቬለ ተናግረዋል። የግንባሩ ሊቀመንበር በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ጥብቅ ቁጥጥር ስር መሆናቸው በዕለት ተዕለት ስራቸው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩንም አቶ ቀጄላ ተናግረዋል።«ባለፈው ጊዜም እንደተነገረው  ከእርሳቸውም አንደበትም የሰማነው ለደህንነታቸው ተብሎ ነው ። ነገር ግን ይሄ ጉዳይ በስራቸው ላይ ቢሮአቸው ለመሄድ ተጽዕኖ አለው»ቀደም ሲል የግንባሩ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ባልተገኙበት በተወሰኑ የስራ አስፈጻሚ እና የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት አማካኝነት ተከናውኖ የነበረው ስብሰባ ዓላማውን ባልተረዱ ሰዎች የስም ማጥፋት ዘመቻ ተካሂዶበት በግንባሩ ላይ ብርቱ ጉዳት ማስከተሉን አቶ ቀጄላ ተናግረዋል።«አሁን ከስብሰባው ጋር በተያያዘ በተፈጠረው ውዥንብር ብዙ ጥፋት ተከስቷል። መጠነ ሰፊ የፕሮፖጋንዳ ዘመቻ ሲከፈት ነበር። በስብሰባው ላይ የተሳተፉትን ሁሉ በጠላትነት የመፈረጅ ስራ ውች ሀገር ባሉ በግንባሩ አባላት እና ደጋፊዎች ሲከናወን ቆይቷል። «አንዳንድ ሰዎች የሚጽፉትን እያየን ነው በጣም አጥፊ ተግባር ነው » በግንባሩ ውስጥ ተፈጠረ ችግርም አቶ ዳውድ ኢብሳ  ወደ መደበኛ ስራቸው ሲመለሱ ሁሉም ነገር በንግግር ይፈታልም ብለዋል አቶ ቀጄላ ፡፡አያይዘውም  አቶ ዳውድ ኢብሳ ዛሬ ወደ መኖርያ ቤታቸው ከተወሰዱ በኋላ ከግንባሩ ምክትል ሊቀመንበር አራርሶ ቢቂላ ጋር መወያየታቸውን ቃል አቃባዩ ተናግረዋል።ዶይቼ ቨሌ ዛሬ ከሰዓቱን ጉለሌ ከሚገኘው የግንባሩ ጽህፈት ቤት አከባቢ እንደተመለከተው በቢሮው መግቢያ በር ላይ የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት ተቀምጠው ከመጠበቃቸው ውጭ ምንም እንቅስቃሴ አላስተዋለም፡፡ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ስዩም ጌቱ በአቶ ዳውድ ስልክ ላይ ደውሎ ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ ተጨማሪ መረጃ ለመጠየቅ ያደረገው ሙከራ  የእጅ ስልካቸው ባለመስራቱ ሳይሳካ ቀርቷል።
ስዩም ጌቱ 
ታምራት ዲንሳ